Saturday, 10 August 2019 00:00

‹‹ወሸን ኦሪቴ›› መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ነዋሪነቱን በእስራኤል ያደረገው የደራሲ አበባው መንግስቴ ዋሴ ‹‹ወሸን ኦሪቴ›› መጽሐፍ ነገ ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ ከማህበረ ቅዱሳን ሕንጻ ፊት ለፊት በሚገኘው ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በዕለቱ እውቅ ገጣሚያንና የስነ-ጽሑፍ ሰዎች ሥራቸውን እንደሚያቀርቡና በመጽሐፉ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቤተ-እስራኤልዊያን የሰንበት ዋዜማ የፀሎት ሥነ-ሥርዓት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለታዳሚያን እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡ … ወሸን ኦሪቴ ኢ - ልብ ወለድ መጽሐፍ ሲሆን ሙሉ ትኩረቱ በቤተ-እስራኤላዊያን ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደሆነና በሺህ ዓመታት ስለዘለቀ የጋብቻ ሥነ -ሥርዓት ወደ እስራኤል የተደረገ ጉዞ (አፕሬሽን ሰለሞን)፣ ዝምድና የተጋረጠበት ጽኑ ፍቅርና ስላስከተለው መዘዝና ቤተ-እስራኤል ከገቡ በኋላ ስለሚገጥማቸው ፈተና ከኢትዮጵያ እስከ እስራኤል በሀሳብ እንደሚያስጉዝ ጋዜጠኛና ደራሲ የኑስ መሃመድ በመጽሐፉ ላይ ባስቀመጠው የጀርባ ማስታወሻ ገልጿል፡፡
በ243 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 3517 times