Saturday, 10 August 2019 00:00

የ”አቦልሴ” ፍሬዎች የግጥም መጽሐፍ ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የገጣሚ እና ጋዜጠኛ ሲሳይ ጫንያለው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ የፊታችን ማክሰኞ ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሲሳይ ከፋና ሬዲዮ ጀምሮ ላለፉት 10 ዓመታት በቆየበት የጋዜጠኝነት ሕይወት ያየውን የተሰማውንና ያጋጠመውን ወደ ግጥም በመቀየር ካከማቻቸው ግጥሞች 80 ያህሉን በመጽሐፉ ማካተቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ተዋንያኑ እታፈራሁ መብራቱና ዓለማየሁ ታደሰ፣ ገጣሚና ሰዓሊ በቀለ መኮንን፣ ደራሲ ሕይወት እምሻው፣ አርክቴክትና ደራሲ ሚካኤል ሽፈራው የሙዚቃ ተመራማሪ ሰርፀፍሬ ስብሃትና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
ገጣሚና ጋዜጠኛ ሲሳይ ጫንያለው ጦቢያ ግጥም በጃዝ ላይ ከሚሳተፉት አንዱ ሲሆን በአሁን ሰዓት በብስራት ኤፍኤም 101.1 ሬዲዮ ላይ “የሁሉ አዲስ” ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

Read 751 times