Saturday, 10 August 2019 00:00

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በገለልተኛ የሙያተኞች አስተዳደር እንዲተካ “ባለአደራው” ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 የአዲስ አበባና የድሬደዋ ም/ቤቶች ምርጫ መራዘሙን በጽኑ የተቃወመው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት አሁን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በገለልተኛ የሙያተኞች አስተዳደር እንዲተካ ጠይቋል፡፡
አሁን ያለው የአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ቤትም ሆነ ም/ከንቲባው ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሥራ አስፈፃሚው የአስተዳደር ዘመኑን ከጨረሰ ሁለት አመት የሞላው ባላደራ ም/ቤቱ በአስቸኳይ ተሰናብቶ፣ ከተለያዩ የሙያ ክፍሎች የተውጣጣ ገለልተኛ የባለሙያዎች አስተዳደር እንዲቋቋም ጠይቋል፡፡
የሚቋቋመው ገለልተኛ የሙያተኞች አስተዳደርም በከተማዋ የፖሊሲና ስትራቴጂያዊ አመራር የሚሰጥ ሳይሆን የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ብቻ የሚሰጥ ሊሆን ይገባል ብሏል - ባለአደራው፡፡
ባለአደራው በተጨማሪ፤ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታዎችን ለሚለቁ የሚከፈል ካሣን ለመወሰን የወጣው አዋጅ፣ በአዲስ አበባ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እስኪመሰረት ተግባራዊ እንዳይደረግና ባዶ መሬት ላይ ማንኛውም አይነት አዲስ ግንባታና የመሬት ምሪት እንዳይካሄድ ጠይቋል፡፡ የተመዘገበው ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት በብድርና በገንዘብ ኖት ህትመት የመጣ ነው

Read 3796 times