ወርሃዊው ሰምና ወርቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት 20ኛው ዙር ‹‹ኢትዮጵያዊነት›› በሚል መሪ ቃል የፊታችን ሀሙስ ነሀሴ 2 በአዲስ አበባ ቴአትር ባህል አዳራሽ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
በምሽቱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች የሚካሄዱ ሲሆን ዶ/ር ብርሃኑ ግዛው፣ አቶ ታዬ ቦጋለ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን፣ መምህር የሸው ተሰማ (የኮተቤው/፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ፣ ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሄር፣ መምህርት እፀገነት ከበደና ገጣሚያኑ ልሳን ሀጎስና ፍፁም ታደሰ በመሶብ ባህላዊ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
Saturday, 03 August 2019 14:26
ሰምና ወርቅ 20ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና