Saturday, 03 August 2019 14:23

ብሌን የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


             የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በየወሩ የሚያካሂደው 7ኛው ዙር ‹‹ብሌን ጥበባዊ የሰላም ምሽት›› የፊታችን ማክሰኞ ሀምሌ 30  ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
በጥበብ ምሽቱ ‹‹ክብረ አበው›› በተሰኘው መርሃ ግብሩ ሦስት የጥበብ አንጋፋዎችን የሚያከብር ሲሆን ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ፣ ደራሲና ሀያሲ አስፋው ዳምጤና ደራሲና ተርጓሚ ሳህለ ስላሴ ብርሃነ ማሪያም መሆናቸውን ገልጿል::
በተጨማሪም በደራሲያንና በታዋቂ ግለሰቦች የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ያስታወቀው ማህበሩ፤ ሙሃዝ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ አንጋፋው ጋዜጠኛና አርታኢ  ጥበቡ በለጠ፣ ገጣሚያኑ ደምሰው መርሻ፣ ህሊና ደሳለኝ፣ ሰይፉ ወርቁና ሌሎችም ስራዎቻቸውን በማቅረብ እንደሚሳተፉ ጠቁሟል፡፡

Read 493 times