Saturday, 09 June 2012 10:34

“ግጥምን በጃዝ” ረቡዕ ይካሄዳል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በወጣት ገጣሚያን እና ሙዚቀኞች የሚንቀሳቀሰው “ግጥምን በጃዝ” አስራ አንደኛ ዝግጅቱን በመጪው ረቡዕ ምሽት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ከቀደምት ፀሐፍት ግጥሞች በሚያቀርብበት ዝግጅት አርቲስት ግሩም ዘነበ ትወና፣ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም ወግ፣ እንዲሁም ለዝግጅቱ አዲስ የሆኑ ገጣሚያን ይርጋ ገላው እና ጌታቸው ይመር የግጥም ሥራዎቻቸውን ከሌሎች አቅራቢዎች በመሳለጥ ያቀርባሉ፡፡ የኪነጥበብ ዝግጅቱ የመግቢያ ትኬት በሰው 50 ብር ነው፡፡

 

 

Read 1233 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:42