Saturday, 03 August 2019 13:40

“ግጥም በኛ” የግጥም ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)


            በጀርመን የባህል ማዕከል የተዘጋጀውና በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚቀርበው “ግጥም በኛ” የተሰኘ የግጥም ምሽት፤ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትር ባህል አዳራሽ ይካሄዳል::
የግጥም መሰናዶው በጋሞኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ጌዲኦኛ፣ ሲዳምኛ፣ ወላይትኛ፣ ኦሮምኛና ጉራጊኛ ቋንቋዎች የሚቀርብ ሲሆኑ፤ ገጣሚያኑ አድማሱ ቱማቶ፣ ዓሊ አብደላ፣ ባጢሶ ዮሐንስ፣ ፍቃዱ ንጉሴ፣ ጌቱ በቀ፣ለ ካፖ ሳንካ፣ ሙሉ ጉድፋይና፣ ተስፋዬ ጐይቴ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ በምሽቱ ሙዚቃና ሌሎች ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች እንደሚቀርቡና ግጥሞቹ ከነለዛቸው በአማርኛ በትናንሽ መጽሔት መታተማቸውን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ታረቀኝ የገለፁ ሲሆን መግቢያ በነፃ ነው ተብሏል፡፡

Read 1357 times