Saturday, 03 August 2019 13:35

ሚሊዮኖች በሳይንሳዊ መንገድ ተወለዱ፡፡ ይወለዳሉም

Written by 
Rate this item
(0 votes)


            እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ Steptoe እና Edwards የተባሉ ሳይንቲስቶች የእንስሶችን እንቁላል ከእንስሶቹ ሰውነት ውጭ የማዳቀል ስራ ጀምረው ነበር፡፡ ከዚህም በመነ ሳት ሰዎችም በዚህ መንገድ ልጅ እንዲያገኙ ማድረግ ይቻላል ብለው ቢያምኑም በሳይንሱ አለም ያሉ ሰዎችን ጨምሮ የብዙዎችን ድጋፍ ግን ማግኘት አልቻሉም ነበር፡፡ ከሰዎች የዘር ፈሳሽን እና እንቁላልን በላቦራቶሪ በማዳቀል ከዚያም ልጅ እንዲወለድ ማድረግ ሞራል የሚነካ እና በሰው ላይ ሊፈጸም የማይገባው ኢሰብአዊ ድርጊት ነው ተብሎ በመወሰዱ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸው እውቅናና ድጋፍ ሳያገኙ ድርጊቱም ከእንስሶች ሳያልፍ ቆይቶአል፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን መረጃ ይፋ ያደረገው The Guardian የተሰኘው ጋዜጣ ነበር ነገሮች መለወ ጣቸውን በሚያበስር መልኩ የዛሬ ስድስት አመት የመጀመሪያውን በሳይንሳዊ መንገድ ተረግዞ የተወለደውን ሉዊስ ብራውንን የጨቅላ ፎቶ ይዞ የወጣው ፡፡ በጁላይ 12/2013 አርብ ቀን ለንባብ የበቃው ጋዜጣ እንደገለጸው ሉዊስ የተወ ለደው በ1978/ዓም ሲሆን በጊዜው በጋዜ ጣው በወጣበት ቀን እድሜውም 35 ደርሶ ነበር፡፡ ይህንን ድንቅ የላቦራቶሪ ውጤት እውን ያደረጉት ሳይንቲ ስት Robert Edwards እና የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑት Patrick Steptoe ናቸው፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ልጅን ባለማግኘት ረገድ የሚሰቃዩ ሰዎች ከዚህ በሁዋላ ሊቸገሩ አይገባም መፍትሔ አለ በማለት ደስታን ያበሰሩ ምርጥ ባለሙያዎች ናቸው ይላል The -Guardian.
በዚያን ወቅት በላቦራቶሪ ተዳቅሎ ወደ እናቱ ማህጸን በመግባት ጊዜውን ጠብቆ የተወለደው ሉዊስ 35 አመት እድሜውን ያስቆጠረ ሲሆን ሳይንሳዊ ድርጊቱ ወደፊት በመቀጠል ሌሎች በተፈጥሮአዊ መንገድ መውለድ ያቃታቸው ሰዎች ተጠቅመውበት በዚያን ጊዜ በአለም ላይ አምስት ሚሊ ዮን ያህል ህጻናት እንዲወለዱ ያስቻለ መሆኑን በጊዜው ይፋ ሆኖአል፡፡
የመጀመሪያው የ IVF ውጤት የሆነው ሉዊስ በ2018 ዓ/ም አርባ አመት ልደቱ የተከበረለት ሲሆን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2100/ በዚህ ሳይንሳዊ ዘዴ የሚወለዱ ልጆች የአለምን 3.5 % ማለትም ወደ 400/ሚሊዮን ይደርሳሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ሉዊስ 40 አመት ልደቱ በተከበረበት ወቅት ሌሎች ስድስት ሚሊዮን ልጆች በአለም አቀፍ ደረጃ እንደተወለዱ ተጠቁሞ አል፡፡ ከአርባ አመት በፊት አወዛጋቢ የነበረው ሳይንሳዊ ልጅ የማዋለድ ዘዴ ዛሬ መልኩን ለውጦ ልጅ ለመውለድ ለተቸገሩ መፍትሔ ሆኖአል፡፡
የመጀመሪያው በላቦራቶሪ እገዛ በ IVF እገዛ የተወለደው ልጅ እድሜ ዛሬ ላይ አርባን የዘለለ ሲሆን ሳይንሳዊ ድርጊቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ እና በይፋ እውን ከሆነ ብዙ የሚባል ጊዜ አይ ጠቀስም፡፡
በዚህ እትም የምናስነብባችሁ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን የ IVF ስራ ይዞ በተፈ  ጥሮአዊ መንገድ ልጅ ማግኘት ያልቻሉትን ሰዎች ልጅ እንዲኖራቸው ለማስቻል በመን ቀሳቀስ ላይ ስላለው NOVA IVI ስለተሰኘው ድርጅት አሰራረ ይሆናል፡፡ ይህ ድርጅት መሰረቱ ህንድ ሲሆን አብሮ አቸው የሚሰራቸው በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የሙያ አጋሮች አሉት:: በኢትዮጵያ ስራውን ሲሰሩ ያገኘናችው ከህንድ BYJU NAIR (በአፍሪካ የአለም አቀፍ የሽያጭ ማናጀር) እና ከኢት ዮጵያ ቤተል ተካ የተባሉ የድር ጅቱ ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ NOVA IVI በአለም አቀፍ ደረጃ ከብዙ ሀገራት ጋር ይሰራል፡፡
ባለሙያዎቹ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ ልጅ መውለድ አልቻልንም ብለው ለእርዳታው የሚመጡ ሰዎችን በሁለት መንገድ የሚያገኙ ሲሆን የመጀመሪያው መንገድ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞችን በሳምንት ሶስት ቀን ባሉበት እየሄዱ በማናገር ልጅ መውለድ ያልቻሉ ሰዎች ሲገጥ ሙአቸው ወደ እነሱ እንዲልኩዋቸው እና እንዲያማክሩአቸው ማድረግ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በመገናኛ ብዙሀን ስለአገልግሎቱ ትምህርታዊ መልእክት በማሰራጨት ባለጉዳዮቹ ስለ ሕክም ናው እና ስለድርጅቱ በቂ መረጃ እንዲኖራቸው እና ወደ አገልግሎቱ እንዲ መጡ ለማድ ረግ የሚጠቀሙበት አሰራር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጅ ለማዋለድ ስለሚሰራበት ቴክኖሎጂ ለሕ ክምና ባለሙያዎቹም ድርጅቱ ስልጠና እንደሚሰጥ ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡ አገልግሎቱን በሚመለከትም በወር አንድ ቀን ከህንድ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የህክምና እርዳታውን የሚፈልጉ ሰዎችን የምት መለ ከት ዶክተር ያለች ሲሆን ይህች ዶክተር የማህጸንና ጽንስ ሐኪም እና ልጅን በሳይንሳዊ መን ገድ በማዋለዱ ዘዴም ባለሙያ የሆነች ሐኪም ናት፡፡
የህክምናው እርዳታ አሰራርን በሚመለከት ባለሙያዎቹ እንደገለጹት ከሆነ በወር አንድ ቀን ከህንድ አገር የምትመጣው ዶክተር ታካሚዎችን የምትመለከተው በኢትዮጵያ ካሉ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ጋር ነው፡፡ ታካሚዎቹ ያሉበት ደረጃ በደንብ ተፈትሾ በአገር ውስጥ ሊረዱ ከሚ ችሉበት ደረጃ ከሆኑ በአገር ውስጥ እንዲረዱ የሚደረግ ሲሆን ከዚያ በላይ ከሆነ ግን በምን አይነት መንገድ ተዘጋጅተው እና አስፈላጊውን ወጪ ሸፍነው  በመሄድ እርዳታውን ሊያገኙ እንደሚችሉ በግልጽ ተነግሮአቸው ወደ ሕንድ አገር ሄደው በላቦራቶሪው እገዛ ልጅ ማግኘት እንዲችሉ ይደረጋል፡፡ በእርግጥ ለወደፊት ይህ አሰራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያልቅ ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ሂደቱ ሲጠናቀቅ ሙሉ ስራው በሀገር ውስጥ እንደሚያልቅ ባለሙሉ ተስፋ መሆናቸውን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ተገቢውን የህክምና እርዳታ መስጠት ወደ ሚቻልበት ህንድ አገር በመላክ ሰዎቹ ልጅ ማግኘት እንዲችሉ እየተደረገ ነው እንደባለሙያዎቹ ማብራሪያ ፡፡
NOVA IVI በሚሰራባቸው አገራት ከ 25.000 በላይ ሴቶች በተደረገላቸው የላቦራቶሪ እገዛ መሰረት እርጉዝ የሆኑ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ ለእርግዝና ወደሕንድ አገር የሄዱ ከ65/ በላይ ጥንዶች ይቆጠራሉ፡፡ ሁለት ሴቶች መንታ ልጆችን ወልደዋል:: ከአምስት እስከ ስድስት የሚሆኑት አንድ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ከ60% በላይ ደግሞ እርግዝናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ አንዳንዶች ያልተሳካላቸው አሉ፡፡  
ሰዎች በላቦራቶሪ የማዳቀል ዘዴ ልጅ እንዲያገኙ የሚደረግበት ምክንያት የተለያየ ነው፡፡
አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ልጅ መውለድ ለምን እንዳልቻሉ ምክንያቱ የማይታወቅ ሲሆን፤
ሚስትየው እንቁላልዋን በትክክለኛው ጊዜ የመልቀቅ ችግር ካለባት፤
ሚስት ወይንም የሴት ጉዋደኛ የማህጸን በር ችግር (ሕመም) ካለባት፤
ባል ወይንም የወንድ ጉዋደኛ የዘር ፈሳሹን ሲለቅ ትኩረት የማጣት ወይንም ዘግየት የማለት፤
ከላይ በተጠቀሱት እና ሌሎች ምክንያቶች ልጅ መውለድ ላቃታቸው ጉዋደኛሞች ከራሳቸው ማለትም ከወንድየው  የዘር ፈሳሽ እና ከሴትየዋ ደግሞ እንቁላል በመውሰድ በላቦራቶሪ እንዲ ገናኙ ተደርጎ ጽንሱ መፈጠሩ ሲረጋገጥ ወደሴትየዋ ማህጸን እንዲገባ በማድረግ ጊዜውን ጠብቆ እንዲወለድ ክትትል ይደረግለታል፡፡ በእርግጥ ለጊዜው በኢትዮጵያ ያልተጀመረ ቢሆንም ከዚህ ውጭ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ሰዎች በሳይንሳዊው መንገድ ድጋፍ የሚደረግበት ምክንያትም አለ፡፡
ወንዶቸ የዘር ፈሳሻቸው ደካማ እና ጥራት ወይንም ብቃት የሌለው ሲሆን፤
ወንዶች ልጅ ለመውለድ የማያስችል በዘር የሚተላለፍ ሕመም ካለባቸው፤
አንዲት ሴት የትዳር ጉዋደኛ ወይንም የወንድ ጉዋደኛ ከሌላት፤
ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች የዘር ፈሳሹ የማን እንደሆነ ሳይታወቅ ከሌላ ወንድ የዘር ፈሳሽ ተወስዶ የትዳር ጉዋደኛ ወይንም የሴት ጉዋደኛ ልጅ እንድትወልድ የሚደረግበት ሁኔታ አለ፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ባለሙያዎቹ ሲያብራሩ በተለያዩ የማህጸን ወይንም የዘር ማስተ ላለፊያ ቱቦዎች ሕመም ምክንያት ወይንም በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ለረጅም ጊዜ ልጅ ሳይኖራቸው የሚቆዩ ሰዎች መኖራቸውንና ለዚህ እንደመፍትሔ ከሚቆጠሩት መካከል ደግሞ ሳይዘገዩ ሕክምና ማግኘት እና ስለ ሁኔታው ንቃተ ሕሊናቸው እንዲዳብር ማድረግ ከሚጠቀ ሱት መካከል ናቸው፡፡  
አንዲት ሴት እድሜዋ ከ50/ አመት በላይ ከሆነ ወይንም የባልና ሚስት እድሜ በድምሩ ከ100/ አመት በላይ ከሆነ በላቦራቶሪ እገዛ ልጅ ለመውለድ የሚደረገው ሂደት አይከናወንም፡፡እድሜያ ቸው ከተጠቀሰው በታች ከሆነ ግን እድሉን እንዲሞክሩ እንደሚደረግ NOVA ዎች ገልጸዋል፡፡
NOVA IVI የተሰኘው ልጅን ላጡ ልጅ እንዲያገኙ በሳይንሳዊ መንገድ የሚሰራው ድርጅት ከተገልጋዮቹ የሚጠይቀው የህክምና ወጪ ከባድ አለመሆኑንና ልጅን ማግኘት ካለመቻል በላይ ምንም የሚከብድ ነገር እንደሌለም ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡


Read 13282 times