Saturday, 09 June 2012 10:33

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 2500 መፃሕፍት በእርዳታ አገኘ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ባህል ጥናት ትምህርት ክፍል በእንግሊዝ ይኖሩ ከነበሩት ዶ/ር ሚካኤል ኢያሱ 2500 መፃሕፍትን በእርዳታ አገኘ፡፡ አሁን በሕይወት የሌሉት የኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ ምሩቅ ዶ/ር ሚካኤል ኢያሱ ከሰጧቸው መፃሕፍት አብዛኞቹ የፍልስፍና ናቸው፡፡ ለመፃሕፍቱ በእርዳታ መገኘት ምክንያት የሆኑት የዩኒቨርሲቲው ታሪክና ባህል ጥናት ድህረ ምረቃ አስተባባሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ በከሬ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ ምልልስ “መፃሕፍቱን ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ከወጣው አራት ሺህ ፓውንድ እና ሀገር ውስጥ ከገባ በኋላ ለጉምሩክ የተከፈለውን ጨምሮ የመጋዘን ኪራይ 120ሺህ ብር ፈጅቶብናል፡፡

መፃሕፍቱ እዚህ እስኪደርሱ አንድ አመት ፈጅቷል፡፡” ብለዋል፡፡ እነዚሁ መፃሕፍት የዶ/ር ሚካኤል ልጅ ሃና ሚካኤል ከሌሎች የክብር እንግዶች ጋር በተገኘችበት በመጪው ሐሙስ ርክክብ የሚደረግ ሲሆን የዩኒቨርስቲው አዲስ ቤተመፃሕፍት አንድ ክፍል በዶክተሩ እንደሚሰየም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

 

Read 1236 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:40