Saturday, 09 June 2012 10:28

ለአውስትራሊያዊው መሸኚያ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በስኬት ተጠናቀቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” የሙዚቃ ክሊፕ ላይ ጣሊያኒያዊ ገፀ ባህርይ በመወከል የተሳተፈውን የአውስታራሊያ ተወላጅ ስላቪኮ ባለስኪ ለማመስገንና ወደሃገሩ ለመሸኘት የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የስእል ኢግዚቢሽን ላይ ከቀረቡት አስር ስዕሎች ስምንቱ እንደተሸጡ የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅና የሳቢሳ ፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤት ተስፋዬ ወ/አገኝ ገለፀ፡፡ አርቲስት አበባ ባልቻና የአዲካ ባለቤት አቶ አዋድን ጨምሮ ስምንት ግለሰቦች አንዱን ስዕል በ20ሺ ብር እንደገዙት ታውቋል፡፡ ገንዘቡ የተሰባሰበለት አውስትራሊያዊ በችግር የተነሳ ወደ አገሩ መሄድ እንዳልቻለ የጠቀሰው የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅ፤ አሁን በክብር ተመስግኖ ወደ አገሩ እንደሚሸኝ ተናግሯል፡፡

 

 

Read 790 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:32