Print this page
Saturday, 27 July 2019 12:42

የአንጋፋው ከያኒ ደበበ እሸቱ 75ኛ የልደት በዓል ሀምሌ 28 ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ልደቱን አስመልክተው 75 ሰዎች የአይን ብሌን ልገሳ ቃል ይገባሉ

           የአንጋፋው ከያኒ ደበበ እሸቱ 75ኛ ዓመት የልደት በዓል በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ሀምሌ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል በድምቀት ይከበራል፡፡
የልደት አከባበሩ ኮሚቴ ከትላንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ ካዛንቺስ በሚገኘው አፍሮ ዳይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ፣ የአርቲስቱን ልደት በማስመልከት ከ75 በላይ ሰዎች የአይን ብሌን ልገሳ ቃል ኪዳን የሚገቡ ሲሆን፣ ደበበ እሸቱ ከአንጋፋው ማንያዘዋል እንደሻው ጋር በመሆን የፊታችን ሀሙስ ሀምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ 75 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የቴአትር ፍላጎት ላላቸው የቴአትር ወርክሾፕ እንደሚሰጥም ታወቋል፡፡
ሀምሌ 28 ምሽት በሚካሄደው የልደት አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ በአርቲስቱ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ ደጀኔ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም፣ ስለአርቲስቱ የተገጠሙ ግጥሞችና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ ለምሽቱ የተዘጋጀውን የክብር  የእራት ግብዣ የሚሸፍነው ሸራተን አዲስ ሆቴል መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 6994 times