Saturday, 27 July 2019 12:43

‹‹ሰቆቃወ ዘዩግ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


            በደራሲ ዘርዓሰብ ሳጌጥ የተሰናዳውና ወጎችና አጫጭር ታሪኮችን ያካተተው ‹‹ሰቆቃው ዘዩግ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ መጽሐፉ በዋናነት አገራችን ላይ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ውጥንቅጥ ተከትሎ ዜጎች የሚደርስባቸውን ስቃይ የሚያሳይ ሲሆን (ዘ ዩግ) የሚለው ቃልም ትርጉም መዜግ ወይም ዜጋ መሆን የሚል ሲሆን መጽሐፉ ‹‹ሰቆቃወ  ዘ ዩግ›› የተባለበትም በአገር ኗሪነት  ያለውን ስቃይና ሰቆቃ ያመለክታል ተብሏል፡፡
መጽሐፉ በሁለት ክፍሎች የተሰናዳ ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል ወጎችና መጣጥፎች በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አጫጭር ታሪኮች መካተታቸውም ታውቋል፡፡  
በ219 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፍ በ100 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራው ከዚህ ቀደም ‹‹ጌርሳም›› (የባይታዋር ገድል) የተሰኘና የ2010 ዓ.ም የሆሄ ስነ ፅሑፍ ሽልማት እጩ የነበረ እንዲሁም ‹‹እግዜር እንቆቅልህ›› የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፎችን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 6717 times