Print this page
Saturday, 09 June 2012 10:18

“ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” በገቢው “አቬንጀርስን” ይፎካከራል ተባለ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በ250 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” ከአምስት ሳምንት በኋላ ለገበያ ሲበቃ ከፍተኛ ገቢ ሊኖረው እንደሚችል ተገምቷል፡፡ በፊልሙ ላይ የባትማን ገፀባህርይ  የሚተውነው ክሪስትያን ቤል ሲሆን አና ሃታዌይ ፤ ቶም ሃርዲ፤ ማይክል ኬን፤ ጋሪ ኦልድማን፤ ሊያም ኔሰንና ሞርጋን ፍሪማን ሌሎች እውቅ የፊልሙ ተዋናዮች ናቸው፡፡ በ3ዲ ለእይታ የሚበቃው ፊልሙ፤ በተወዳጅነትና በገቢው ከፍተኛነት የዓመቱ መሪ ሊሆን እንደሚችል ሲገመት “ዘ አቬንጀርስ” ዘንድሮ ያሳካውን ገቢ ለመስተካከል ግን እንደሚቸገር የፎርብስ መፅሄት ትንተና አመልክቷል፡፡

እንደ ፎርብስ ሪፖርት “ዘ አቬንጀርስ” እና “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” የጀምስ ካሜሮን “አቫታር” በመላው ዓለም 2.78 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስመዝግቦ በከፍተኛ ገቢ የምንግዜም ምርጥ ፊልም በመሆን የያዘውን የመሪነት ስፍራ ለመስተካከል ያዳግታቸዋል፡፡ ይሁንና “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” በገቢ ስኬቱ የምንግዜም ከፍተኛ ገቢን ካስገቡት 10 ፊልሞች ተርታ ለመግባት እድል ሊኖረው ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት የፊልሙ የመጀመርያ ክፍል “ዘ ዳርክ ናይት” በመላው ዓለም 1.3 ቢሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡

 

 

 

 

Read 887 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 10:23