Saturday, 20 July 2019 12:23

የአእምሮ ጤና ከወሲባዊ ትንኮሳ…ጥቃት አንጻር

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

 ወሲባዊ ትንኮሳ ማለት ምን ማለት ነው?
ወሲባዊ ትንኮሳ ካለ መጨረሻው ወሲባዊ ጥቃት ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለቱም ትርጉዋሜዎች የሚ ገልጹት ፈቃደኝነትን መሰረት ያላደረጉ አንዱ በአንዱ ላይ ማለትም ወንድ በሴት ላይ ወይንም ወንድ በወንድ ላይ በማስገደድ፤ በማባበል፤ ወይንም በጉ ልበት የሚፈጽሙት ድርጊት ስለሆነ እና ልዩነታቸውም የጎላ ስላልሆነ ሁለቱም አንድ አይነት ተብለው ሊተረጎሙም እንደሚችሉ ባለሙ ያዎች ይገልጻሉ Good Therapy በተሰኘው መረጃ  እንደተጠቀሰው፡፡
ወሲባዊ ትንኮሳ ወይንም ጥቃት ሲባል…
ያልተፈለገ ወሲባዊ ግንኙነትን መፈጸም ወይንም ለመፈጸም  በራስ ፍላጎት ብቻ በመመስረት መንገዶችን ለማመቻቸት ወይንም ለመፈጸም መሞከር፤
ሰዎችን በግል የወሲብ ሕይወታቸው ጣልቃ በመግባት አስተያየት፤ ትችት፤ ቀልድ የመሳሰሉትን ነገሮች በመናገር ባላሰቡት እና ባላቀዱት መንገድ ለወሲብ ድርጊት እንዲገፋፉ ማድረግ፤ቀጠሮ ማስያዝ የመሳሰሉትን ይመለከታል፡፡
ወሲባዊ ጥቃት የትም ቦታ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ሰው ሊፈጸም የሚችል ጎጂ ነገር ነው:: ቢሆንም ግን በብዙ ሀገሮች እንደታየው ከሆነ ወሲባዊ ትንኮሳንና ጥቃትን በሚመለከት በተለይም በስራ ቦታዎች እንዳይፈጸሙ ለማድረግ የወጡ ህጎች ስራ ላይ ውለዋል፡፡ በስራ ቦታ ዎች የሚፈጸሙ ወሲባዊ ትንኮሳዎች ወይንም ጥቃቶች፤ በአይን በመተያየት፤ በእጅ በመነካ ካት፤ ስለስራ በማውራት፤ አለቃና ሰራተኛ በመሆን ወይንም ትእዛዝ በመስጠትና በመቀበል፤ የግል የህይወት ወይንም የኑሮ ገጠመኞችን በሚመለከት መሸፋፈን የመሳሰሉትን  ምክንያት በማድረግ መላመድ ስለሚኖር ትንኮሳ ወይንም ጥቃቱ የሚደርስበት ሰው ባላሰበው መንገድ የሚፈጽመው ሊሆን ይችላል፡፡ምግብና መጠጥ መጋበዝ…አንዳንድ ያልተጠበቁ ስጦታዎችን ማበር ከት… የመሳሰሉት ድርጊቶች ይከወናሉ፡፡ ጾታዊ ጥቃት አድራሽና ተጠቂ ከነበራቸው ቅርርብና የስራ ግንኙነት የተነሳ ጉዳዩን ግልጽ ከማድረግና ፍትሕ ከመፈለግ ይልቅ በእፍረት ዝም ማለትን ስለሚመርጡ ድርጊቱ ውስጥ ውስጡን እየሰፋ ይሄዳል፡፡
በሕጻናት ላይ የሚደርስ ወሲባዊ ጥቃት፤
በህጻናት ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት በብዙ መንገድ የሚገለጽ ነው፡፡ አንዳድ ጊዜ በኃይል ቅርብ ባልሆነ ወይንም በማይታወቅ ሰው ሊሆን ሲችል አንዳንድ ጊዜ ቅርብ በሆኑ ቤተሰቦች አማካኝነት ሊሆን ይችላል፡፡ ሕጻናት ወሲባዊ ጥቃት ሊደርስባቸው ቀርቶ አካሎቻቸው እንዲነኩ አንኩዋን እንደማይፈልጉ ግልጽ ነው፡፡ ለምሳሌ ልጆች ገላቸውን በሚታጠቡበት ጊዜ ወይንም ልብሳቸውን በሚቀይሩበት ጊዜ የሚረዱዋቸው ሰዎች አላስፈላጊ መነካካት ካደረጉ በልጆቹ ላይ እንደደረሰ ወሲባዊ ትንኮሳ ይቆጠራል፡፡ የዚህን ድርጊት ጎጂነት ልጆች በቀላሉ ሊረዱት የማይ ችሉት በመሆኑ ለጥፋቱ የተሰማሩ አዋቂዎች ልጆቹን በማባበልና ፈቃደኛ እንዲሆኑ በማድረግ ሊፈጽሙት እንደሚሞክሩ ግልጽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ልጆችን ለድርጊቱ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ማድ ረግ ጥፋቱን እንዲፈጽሙ ፈቃድ ማግኘት አይደለም፡፡ ምንም እንኩዋን ልጆቹ የሚከተለውን ነገር ካለማወቅ መጀመሪያ ዝምቢሉም በሁዋላ ድርጊቱ የሚፈጸመው በኃይል ድርጊት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ህጻናቱ ውጤቱን ስለማያውቁት ለተፈጸመው ነገር ስምምነት አድርገዋል ለማለት ከእድሜያቸውም አንጻር አይቻልምስ ፡፡   
በብዙ ሀገራት እንደታየው ልምድ ከሆነ ህጻናቱ የወሲብ ተጠቂ መሆናቸውን ለማንም ግልጽ አድርገው መናገር እንደማይፈልጉ ነው፡፡ የዚህም ምክንያት ጥቃት አድራሾቹ ህጻናቱን ስለሚያ ስፈራሩዋቸው ነው፡፡ Good Therapy የተሰኘው መረጃ እንደሚገልጸው ጥቃት ከደረሰባቸው ህጻናት ወደ 93% የሚሆኑት ጥቃት ያደረሱባቸውን ሰዎች በደንብ የሚያው ቁዋቸው እና ድርጊቱን ግን ለቤተሰብም ሆነ ለማንም እንዳልተናገሩት መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ነው፡፡ በአሜሪካ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው…
73%የሚሆኑ ህጻናት የደረሰባቸውን ትንኮሳ ወይንም ጥቃት ለአንድ አመት ወይንም ከዚያ በላይ ይደብቁታል፡፡
45%የሚሆኑ ህጻናት ከአምስት አመት በላይ ለሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ ድርጊቱን ጭርሱንም ላይናገሩት ይችላሉ፡፡
ምንም እንኩዋን በህጻናት ላይ የደረሰውን ወሲባዊ ጥቃት ከልጆቹ መስማት እና በጊዜው ማወቅ ባይቻልም ልብ ብሎ ህጻናቱን ትኩረት በመስጠት መከታተልና ማየት ጠቃሚ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምልክት የሚሆኑ ነገሮች ይታያሉ፡፡
የውስጥ ልብስ መቀደድ ወይንም አንዳንድ ምልክት ማሳየት
ሽንትን ቶሎ ቶሎ መሽናት ወይንም infection መመረዝ ማሳየት
በመኝታ ሰአት መቃዠትና መጨነቅ
በመኝታ ላይ ሽንትን መልቀቅ
ቁጣና መረበሽ
ከሌላ ሰው ሰውነት ጋር እንዳይገናኙ መሻት
መደበርና ከምንም ነገር ተሳትፎ መታቀብ
ከእድሜአቸው በላይ ስለወሲባዊ ግንኙነት ማወቅ …ወዘተ
በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በእርግጠኝነት የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናት የሚያሳዩአቸው ምልክቶች ናቸው ማለት ባይቻልም ጉዳቱ የደረሰባቸው ህጻናት ግን የሚያሳ ዩአቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ ወላጆች ወይንም የልጆች ተንከባካቢዎች አብረዋቸው ያሉ ህጻናትን ሁኔታ ለማወቅ ቸል ሳይሉ እለት ተእለት ስለ አለባበሳቸው፤ ስለ ንቃታቸው፤ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ፤ ስለጤንነት ሁኔታቸው፤ ስለ ትምህርት ክትት ላቸው…ወዘተ ልጆቹ በግልጽ በሚያውቁትም ሆነ በማያውቁት ሁኔታ ጭምር አበክረው ሊፈ ትሹ ይገባል፡፡ በተለይም ግልጽ ውይይትን የማዳበር ልምድን ልጆቹ አስቀድሞውኑ እንዲ ያውቁ ቢደረግ የወሲብ ጥቃት ሲደርስባቸውም ምንም እንኩዋን ጥቃት አድራሹ ቢያስፈ ራራቸውም ለወላጆቻቸው ከመንገር ወደሁዋላ አይሉም፡፡ ልጆቹ የደረሰባቸውን ጥቃት ለወላጅ ወይንም በቅርብ ለሚወዱት ፤ለሚያ ቀርቡት ሰው ቢናገሩ በግልጽ ከሚፈጸመው የፍትህ እና የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ በወ ደፊቱ ሕይወታቸው ሊያጋጥማቸው የሚችለውን የአእምሮ ጤና መታወክ ሊወገድላቸው ይች ላል፡፡ በተጨማሪም የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናት በሚያድጉበት ጊዜ ለአንዳንድ ማለትም መጠጥ፤ አደንዛዥ እጽ፤ ሲጋራ፤ የመሳሰሉትን ጎጂ ነገሮች በወደፊት ሕይወታቸው ሊለምዱ ስለ ሚችሉ ችግሩ እንደደረሰ ወደዚህ አዝማሚያ እንዳይሄዱ የሚያደርጋቸውን አስተዳደግ ሊያገኙ ይገባል፡፡  
በወንዶች ላይ የሚደርስ ወሲባዊ ጥቃት፤
ወንዶች የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑ ከታወቀ የመገለል እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት እንደታየው ከሆነ ወንዶች የወሲብ ጥቃት እንደደረሰባቸው ከታወቀ በቤተሰብ ወይንም በአካባቢው ህብረተሰብ ትክክለኛውን ነገር ሳይረዱ ወንዶቹ ፈልገውት ወይንም ወንዶች ሁልጊዜ የወሲብ ድርጊትን መፈጸም ስለሚወዱ የተፈጸመ መሆኑን በራሳቸው ግምት ያምናሉ፡፡ ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚያምኑት ወንዶች የወሲብ ተጠቂዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
ወንዶች የወሲብ ጥቃት ደርሶብኛል ብለው ለቤተሰብም ይሁን ለሚንከባከባቸው አካል ወይንም ፍትህ፤ ህክምና ቦታ… ወዘተ ለማመልከት ሲፈልጉ የሚፈሩት ተአማኒነትን ነው፡፡ ይህን ብናገር ማን ያምነኛል? የሚለው ጥርጣሬ በውስጣቸው ስለሚያድር ነገሩን አፍነው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ በሌላም በኩል ወንዶች የወሲብ ጥቃት ደረሰብን ቢሉ በራሳቸው ድክመት ወይም ከተመሳሳይ ሰው ጋር ወሲብ መፈጸምን ወድደው እንዳደረጉት እንጂ ተገድደው አይደለም የሚሉ ብዙዎች መሆናቸውን መረጃው ይጠቁማል፡፡ የወሲብ ጥቃትን ወንዶች በወንዶች ላይ ሲያደርሱት ወንዶች በሴቶች ላይ ሲያደርሱት እንደ መግለጽ ቀላል አይደለም፡፡
ከላይ በተጠቀሰው የተሳሳተ ግንዛቤ የተነሳ ወንዶች እራሳቸውን አግልለው የደረሰባቸውን ተገዶ መደፈር ወይንም ጥቃት ለራሳቸው አፍነው በመያዝ ይጎዳሉ፡፡ ስለዚህም ችግራቸውን ለመግ ለጽ ባለመቻላቸው የተነሳ ለብዙ መጥፎ ባህርያት መጋለጥ እና መልካም አሳቢ ሰዎች እንዳ ይሆኑ፤ ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ እሳቤ እንዲኖራቸው ይገደዳሉ፡፡ የፍትህም ሆነ የህክምና እርዳታን እንዳያገኙም ይሆናሉ፡፡ የዚህም ውጤት እራሳቸውን የሚጎዱ ነገሮችን መፈጸም ይሆናል፡፡       
ወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃት በአእምሮ ላይ የሚያስከትሉዋቸው ችግሮች ምንድናቸው?
ይቀጥላል፡፡


Read 9284 times