Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 09:41

ሉሲዎች ለአፍሪካ ዋንጫ አንድ ጨዋታ ቀራቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን   አስፈላጊውን የወዳጅነት ጨዋታ  ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድዬም ከጋና አቻው ሊያደርግ ነው፡፡ በአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውና ጥቋቁር ንግስቶች በሚል ስሙ የሚታወቀው የጋና ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለቅዳሜው ጨዋታ ባለፈው ሀሙስ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡  ሉሲዎቹ ለ8ኛው አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የ1 ጨዋታ እድሜ ቀርቷቸዋል፡፡ ከጋና ጋር የተገኘው የወዳጅነት ጨዋታ ደግሞ የቡድኑን ወቅታዊ አቋም ለመፈተሽ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ከ2 ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ  ስታድዬም  በ2ኛ ዙር የማጣርያ ምእራፍ ሉሲዎች የመጀመሪያ  ጨዋታቸውን አድርገው የታንዛኒያ አቻቸውን 2-1 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ በቀጣይ ዓመት ኢኳቶሪያል ጊኒ ለምታዘጋጀው 8ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ  የዛሬ ሳምንት  ታንዛኒያ ላይ ሉሲዎች እድላቸውን በሁለት ሁኔታዎች ይወስናሉ፡፡

ሁኔታዎቹ ወይ ማሽነፍ ካልሆነም አቻ መውጣት ናቸው፡፡ ሉሲዎች ለለንደን ኦሎምፒክ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው  በደቡብ አፍሪካዎቹ ሴቶች ያጡትን  እድል በአፍሪካ ዋንጫ እንደሚያካክሱ ሲጠበቅ በመልስ ጨዋታ ዳሬሰላም ላይ ከተሳካላቸው በታሪካቸው ለ3ኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ይችላሉ፡፡ የታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በአዲስ አበባው ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ለመሸነፍ ባለመፈለጋቸው ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለባቸው ተግባራት ፈፅመውብናል በሚል ለታንዛኒያ ጋዜጦች አማርረዋል፡፡ አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድናቸው  አዲስ አበባ ላይ ስታድዬም ውስጥ በመልበሻ ክፍል በገጠመው ከፍተኛ የኬሚካል ሽታ መቃወሱን ሲያማርሩ ተጨዋቾች በመልበሻ ክፍልነት የስታድዬሙን ኮሪደር ለመጠቀም መገደዳቸውን ገልፀው ሁኔታው በውጤታቸው ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ የታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድን አባላት  በዳሬሰላም የሚያስተናግዱትን የመልስ ጨዋታ የተቻላቸውን መስእዋትነት ሊከፍሉበት እንደተዘጋጁ ሲናገሩ ለሁለተኛ ግዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን  በሜዳቸው ለመወሰን ቁርጠኛ መሆናቸውን  እየገለፁ ናቸው፡፡ በመልሱ ጨዋታ የታንዛኒያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በቱርክ በሚገኝ ክለብ የምትጫወተውን ሙኩዋሲ የተባለች የተከላካይ መስመር ተጨዋች ለማሰለፍ መቻላቸውም የማለፍ ተስፋቸውን እንዳጠናከረ የአገሪቱ ሚዲያዎች ሰሞኑን ዘግበዋል፡፡

 

ከ2 ሳምንት በፊት ሉሲዎች ከታንዛኒያ እህትማማቾች ጋር በመጀመርያ ጨዋታው አዲስ አበባ ስታድዬም ላይ ሲገናኙ ጨዋታው በተጀመረ በ19ነኛው ደቂቃ ታንዛኒያዎች ግብ በማስቆጠር መሪነቱን ይዘው ነበር፡፡ በሜዳቸው በእንግዳው ቡድን 1ለ0 መመራት የጀመሩት ሉሲዎች በተደጋጋሚ የግብ ሙከራ ማድረጋቸው ሲታወስ ይህ ጥረታቸው ያስገኘውን  ፍፁም ቅጣት ምት ሄለን ሰይፉ አስቆጥራ የመጀመሪያው ግማሽ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡  በሁለተኛው ግማሽ ሉሲዎች በማጥቃት ላይ በተመሰረተ አጨዋወት ከፍተኛ ብልጫ በማሳየት ለማሸነፍ ከፍተኛ ትግል ሲያደርጉ ቆዩ፡፡ በመጨረሻም  ተቀይራ በገባችው ቱቱ  በላይ አማካኝነት ሁለተኛውን  ጎል በማስቆጠር ሉሲዎች 2ለ1 የታንዛኒያ አቻቸውን  ማሸነፋቸው አይዘነጋም፡፡

 

 

Read 1836 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 09:46