Saturday, 20 July 2019 12:10

በዘነበ ወላ የተፃፈው “የምድራችን ጀግና” መጽሐፍ ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 
    በሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገ/እግዚብሔር የህይወት ታሪክ እና ስራ ላይ ያተኮረውና በዘነበ ወላ የተፃፈው “የምድራችን ጀግና” መጽሐፍ ማክሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ ሎሬቱ እና የቀድሞ ተማሪዎች፣ ወዳጆች እና የስራ ባልደረቦችን ጨምሮ ታዋቂ ገጣሚያንና ደራሲያን ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ዶ/ር በድሉ ዋቅራ፣ ኤፍሬም ስዩምና ዶ/ር ሱራፌል ወንድሙ በእለቱ የግጥም ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የምርቃቱ አዘጋጅ አዳነ መታሰቢያ የማስታወቂያ ስራ ድርጅት አስታውቋል፡፡

Read 7287 times Last modified on Saturday, 20 July 2019 12:40