Saturday, 20 July 2019 11:46

ዘንድሮ 163 የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 በዘንድሮ አመት በኢትዮጵያ ውስጥ በስደት ላይ የሚገኙ 163 የተለያዩ ሀገራት ዜጐች በአገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የነፃ ትምህርት እድል አግኝተው፣ በድግሪ መመረቃቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል፡፡
ስደተኞቹ በብዛት ከኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ የመጡ መሆናቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ 137 ተማሪዎች በጀርመኑ የአልበርት አንስታይን አካዳሚ የስደተኞች ድጋፍ ነፃ የትምህርት እድል አግኝተው የተማሩ ሲሆን ቀሪዎቹ 26 ያህሉ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ የትምህርት እድል የሰጣቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ስደተኞቹ በህብረተሰብ ጤና፣ በህግ፣ በእንስሳት ህክምና፣ በኢንጂነሪንግ እና በትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቁ ናቸው ተብሏል፡፡ ተማሪዎቹን ተቀብለው ያስተማሩ ዩኒቨርስቲዎችም፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ፣ ጋምቤላ፣ ሃረማያ፣ አሶሳ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የሚሰጡ የነፃ የትምህርት እድሎች ስደተኞችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የጠቆመው የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ማዕከሉ፤ ህፃናትም በስፋት የትምህርት እድል እያገኙ ነው ብሏል፡፡

Read 6589 times