Saturday, 13 July 2019 11:05

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ እና አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ይቀበላሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት የሚያስመርቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ለኢትዮጵያ እስላማዊ ም/ቤት (መጅሊስ) ዋና ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ሁመር ኢድሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም  የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር የክብር ዶክትሬቱን የሚሰጠው ለህዝብ ሠላምና አንድነት ላበረከቱት የእድሜ ዘመን አገልግሎት ነው ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አየር መንገዱን የላቀ ውጤታማ በማድረጋቸው የክብር ዶክትሬት ባለቤት እንደሚሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የክብር ዶክትሬቱ እንዲሰጣቸው ማመልከቻ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደሆኑ  ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢንድሪስ ደመቀ በወሎ ክ/ሀገር ለጋምቦ ወረዳ ገነቴ በምትባል መንደር ግንቦት 21 ቀን 1929 የተወለዱ ሲሆን በእስልምና እምነት መምህርነታቸውና መሪነታቸው ይታወቃሉ:: ከ50 በላይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍት እንደፃፉም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Read 1593 times Last modified on Tuesday, 16 July 2019 10:25