“ሕዝቦችን ሁሉ የሚፈጥር አንድ አምላክ ነው:: ይህም አምላክ የምንለው የሕዝቦች ፈጣሪ፤ ሕዝቦቹን ሁሉ ትክክል አድርጎ ፈጥሮ ላኗኗራቸውና ለልማታቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ከሙሉ ፈቃድና ሥልጣን ጋራ በጃቸው ሰጥቷቸዋል:: ስለዚህ ማናቸውም ሕዝብ ቢለማም ቢጠፋም በገዛ እጁ ነው፡፡
ሕዝብ የሚጠፋበት አንዳንድ ጊዜ ምክንያት ቢገኝ፤ ያውም ምክንያት ባንዳንድ ሰው ቢመካኝ፤ ነገሩ ትክክል አይሆንም፡፡ የልማትን መንገድ ለማግኘት የሚጥር ሕዝብ ቢገኝ፤ ባንዳንድ ክፉ ሰው ምክንያት ሊጠፋ አይችልም፡፡ እንዲሁም ደግሞ የልማትን መንገድ ለማግኘት የማይጣጣር ሕዝብ ባንዳንድ ደኅና ሰው ኃይል ልማት ሊያገኝ አይችልም:: ደግሞም ማናቸውም ሕዝብ የሚለማበት መንገድ አንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ማናቸውም ሕዝብ የሚጠፋ ይህንን የልማት መንገድ ትቶ በሌላ መንገድ የሄደ እንደሆነ ነው፡፡ “
ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ
Published in
ባህል
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል