Saturday, 06 July 2019 14:15

“በገሃነም ስር መፅደቅ” የግጥም መድበል ለአንባቢ ቀርቧል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)


           የጋዜጠኛ ዘላለም ገበየሁ ሁለተኛ ስራ የሆነው “በገሃነም ስር መፅደቅ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
ግጥሞቹ በወቅቱ የፖለቲካ ምስቅልቅል፣ በምስቅልቅሉ ውስጥ ስላለው የተስፋ ጭላንጭል፣ የለውጡ ስጋቶችና ተስፋዎች-- ላይ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ መድበሉ ከ50 በላይ ግጥሞችን  አካትቷል፡፡ 64 ገጾች ያሉት የግጥም መድበሉ፤በ49 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘላለም ገበየሁ፤ ከዚህ ቀደም “ዳሞትራ” የተሰኘ የግጥም መድበል ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 7714 times