Tuesday, 02 July 2019 12:37

የዚህ ዓመት መፅሐፍትን ለማረሚያ ቤቶች የመሰብሰብ ዘመቻ ተጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


      “መፅሐፍትን ለማረሚያ ቤቶችና ለታራሚዎች እንለግስ” በሚል መሪ ቃል በየዓመቱ የሚካሄደው መፅሀፍትን የመሰብሰብ የዘንድሮው ዘመቻ መጀመሩን የሀሳቡ አፍላቂና የዘመቻው አስተባባሪ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር ገበያው ገለፀ፡፡
በዘመቻው የስነ ልቦና፣ የታሪክና የመማሪያ መፅሐፍትን ጨምሮ ማንኛውንም መፅሐፍት የማሰባሰቡ ዘመቻ እንደሚቀጥል ጋዜጠኛው አስታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ዘመቻ የተሰባሰቡ ከ3,500 በላይ መፅሐፍትን ለጅማ፣ ለሀዋሳ፣ ለባህርዳርና ለፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች ማከፋፈላቸውን ሙሉጌታ ገልጿል፡፡
“ዘንድሮ የሚበሰቡትን ለየትኛው ማረሚያ ቤት እንለግስ የሚለውን እንወስናለን” ያለው ጋዜጠኛው፣ ከዘመቻው አንዱ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መግቢያው መፅሐፍ የሆነ የስነ ፅሁፍ ምሽት በማዘጋጀት በርካታ መፅሐፍትን ለማሰባሰብ እንዳቀደ ጋዜጠኛው ጨምሮ ገልጿል፡፡  



Read 4076 times