Saturday, 02 June 2012 10:52

የፑሽኪን 213ኛ ዓመት ልደት ሳምንቱን ይከበራል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የታላቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ሰርጌቪች ፑሽኪን 213ኛ ዓመት ልደት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እንደሚከበር የሩስያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል አስታወቀ፡፡ዝግጅቱ በማዕከሉ የፑሽኪን አዳራሽ፣ ሳር ቤት በሚገኘው የፑሽኪን አደባባይ፣ በሩስያ ኤምባሲ እና በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በሙዚቃ በባሌ ዳንስ እና በሥዕል ውድድር የታጀበ ነው፡፡ ፑሽኪን የተወለደበት እለት፣ ረቡዕ ስለሚውልም በፑሽኪን አደባባይ የአበባ ጉንጉን የሚቀመጥ ሲሆን በአዲስ አበባ ላሉ አምባሳደሮችና ሌሎች ዲፕሎማቶች በሩስያ ኤምባሲ የዳንስ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ የፑሽኪንን ምስለ ራስ የሚያሳይ የሥዕል ውድድር እንደሚኖር የገለፁት አዘጋጆቹ፣ በተጨማሪም  የፑሽኪንን ግጥሞች በአማርኛ፣በእንግሊዝኛና ሩስያንኛ በቃል የማንበብ ውድድር እንዳለም ተናግረዋል፡፡ በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ደግሞ የባሌ ዳንስ እንደሚቀርብ ከሩስያ ኤምባሲ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል የተገኘው መግለጫ ያስረዳል፡፡ ዝግጅቱ “የሩስያ ቋንቋና ባህል በፑሽኪን ሳምንት” በሚል መሪ ቃል የሚቀርብ ነው፡፡

 

 

Read 995 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:55