Sunday, 23 June 2019 00:00

የኢትየጵያ የፋሽን ሳምንት የዛሬ ሳምንት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከአምስት ዓመት በፊት የተቋቋመውና 106 ያህል አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች ማህበር ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ፋሽን ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ 20 ዲዛይነሮች የሰሯቸውን አልባሳት ለታዳሚ እንደሚያቀርቡና የኮክቴል ምሽት እንደሚኖርም የማህበሩ መስራችና ፕሬዚዳንት ትላንት በስካየ ላይት ሆቱል በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚሁ የፋሽን ሳምንት በርካታ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና በምሽቱ ለመታደም 500 ብር የመግቢያ ዋጋ መተመኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 10923 times