Saturday, 02 June 2012 10:48

የግብይትና መረጃ መጽሐፍ ተመረቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የኪነጥበባት እና የማስታወቂያ ድርጅት በየዓመቱ የሚታተመው የግብይትና መረጃ መጽሐፍ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ታትሞ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በሂልተን ተመረቀ፡፡ በ1999 ዓ.ም በአርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያም፣ በኢንጂነር አብይ ፍቃዱ እና በኢንጅነር ብስራት ዳንኤል የተመሠረተው ድርጅት ያስመረቀው መጽሐፍ፤ 856 ገፆች ያሉት ሲሆን 50ሺህ ቅጂ ለቢዝነስ ማህበራትና ለሕዝብ በነፃ ይሰራጫል፡፡ የዚሁ መጽሐፍ ኤሌክትሮኒክ ቅጂ በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ እና ፈረንሳይኛ በድረ ገጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን 100ሺህ ቅጂም በሲዲ እንደተዘጋጀ በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል፡፡መጽሐፉ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች አማካይነት የሚሰራጭ ሲሆን በየሀገራቱ ንግድ ምክር ቤቶች ይቀመጣል፡፡ ከሌሎች መረጃዎች ውጭ መጽሐፉ 100ሺ የንግድ ድርጅቶች መረጃን እንዳካተተ በምረቃው ላይ ተገልጿል፡፡

 

 

Read 633 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:52