Print this page
Saturday, 02 June 2012 10:48

የኪነጥበብ ባለሙያዎች አሊያንስን ሊያመሰግኑ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ፣ ለኢትዮጵያውያን ከያንያን ለሰጠው አገልግሎት  ምስጋና ለማቅረብ ያለመ ኪነጥበባዊ ዝግጅት እንደተሰናዳ ተገለፀ፡፡ “የኪነጥበባት ባለሙያዎች ላከበሩን አክባሪ መሆናችንን ለማሳየትና ከ100 ዓመት በላይ ያገለገለውን አልያንስን ለማመስገን ነው ዝግጅቱን የምናቀርበው” ያለው አርቲስት ዳዊት ፍሬው “የራሳችን ተቋማት ትምህርት እንዲወስዱበት አሊያንስን ማመስገን አስፈልጎዋል” ብሎዋል፡፡ ዝግጅቱ ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተመዘክር በሙዚቃ በታጀበ የሥዕል አውደርእይ እንደሚከፈት ለማወቅ ተችሏል፡፡ መዝጊያው በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ሰኔ 11 እንደሚሆን አርቲስቱ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፆ፣ የሙዚቃ ባለሙያው ሠርፀ ፍሬስብሃት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ አርቲስት ፈለቀ አበበ ግጥም እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡

 

 

Read 857 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:52