Saturday, 02 June 2012 10:43

“በጥበብ ኢትዮጵያ” ላይ ውሳኔ ተሰጠ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በዝግጅታችሁ የዜና ሽፋን ዝግጅታችን አጥላልታችኋል በማለት በእናት የማስታወቂያ ሥራዎች ድርጅት ቅሬታ የቀረበበት “የጥበብና እፎይታ” አዘጋጅ ጥበብ ኢትዮጵያ ለብሮድ ካስት ባለሥልጣን ቅሬታ የቀረበበት ሲሆን ባለስልጣኑም ቅሬታውን ተቀብሎ በማጣራት ውሳኔ ሰጠ፡ “እናት የማስታወቂያ ሥራዎች ድርጅት” ንባብ እንዲያድግ ያዘጋጀሁትን የመፃሕፍት ውድድር እና ሽልማት አስመልክቶ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍ ኤም 98.1 አዲስ አበባ ዘወትር እሁድ ምሽት የሚተላለፈው “ጥበብ እና እፎይታ” የተሳሳተ የማጥላላት ዘመቻ አካሂዶብኛል ብሏል፡፡

ማጣርያ አካሂጃለሁ ያለው ብሮድካስት ባለሥልጣንም ተመጣጣኝ የአየር ሰዓት መድቦ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ለዚህም የሽልማት አዘጋጆችና ዳኞች አስተያየት መካተት እንዳለበትና የማስተባበያ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ውሳኔ መሠራቱም ጭምር እንዲገለፅ እንዲሁም ፕሮግራሙ ከግንቦት 16 ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ እንዲቀርብ ባለሥልጣኑ ወስኗል፡፡ አቅራቢዎቹ በዝግጅት ወቅት ለስህተትና ሕግ ጥሰት አቅራቢዎችንና አድማጮችን ይቅርታ እንዲጠይቁ እና አፈፃፀሙንም ዝግጅታቸውን ባቀረቡ በሦስት ቀናት ለባለሥልጣኑ እንዲያሳውቁ አዟል፡፡ “ብራና” የሚል በንባብ ባህል ላይ የሚሠራ ዝግጅት በኤፍኤም 97.1 እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት የሚተላለፍ ዝግጅት ያለው እናት የማስታወቂያ ሥራዎች ድርጅት በቅርቡ ለንባብ መጎልበት አግዛችኋል በማለት ደራስያንን፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትንና ሌሎችን መሸለሙ ይታወቃል፡፡

 

 

 

 

Read 811 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:45