Saturday, 08 June 2019 00:00

የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ የአንድ ቀን ውሎ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአንድ ቀን ውሏቸው ምን ይመስላል? ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም፡፡ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣጡ 3ሺህ ያህል አቃቢያን ህግና ጠበቆች ጋር ለውይይት ተቀመጡ፡፡
በውይይታቸውም ጠበቆችና አቃቢያን ህግ ስላሉባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ጨምሮ በፍትህ ስርአቱ ላይ አሉ የሚባሉትን ችግሮች በዝርዝር አስረዱ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም፤ መንግስታቸው እንደበፊቱ በፍትህ ስርአቱ ጣልቃ እንደማይገባ ዳግም አረጋገጡ፤ ለፍትህ ስርአቱ መሻሻልም ቁርጠኛ መሆናቸውን አስገነዘቡ፡፡ ስለፍትህና ስለርትዕ በህግ መምራትና በህግ የበላይነት መምራት በዝርዝር ተተነተነ፡፡
ከፍትህ አካላት ጋር ያደረጉት ውይይት ሲጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመሩት ወደ ሌላ ሥራ ነበር፡፡ 78ኛ የምስረታ እድሜው ላይ በሚገኘው ብሔራዊ ቤተመፃሕፍትና ቤተ - መዘክር ተገኙ፡፡
ለፈተና ዝግጅት በጥናት ላይ የነበሩ ተማሪዎችንም አግኝተው አበረታቱ፡፡ ወመዘክርንም ጐበኙ፡፡ ወመዘክርን ካቋቋሙት አፄ ሃይለ ሥላሴ በኋላ ተቋሙን የጐበኙ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ  ያደርጋቸዋል፡፡  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሱዳን ካርቱም የተገኙትም በ24 ሰዓታት የአንድ ቀን ውላቸው ነበር፡፡ በካርቱም የሽግግር ጊዜ ወታደራዊ አመራሮችን ከተቃዋሚዎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ትናንት ሲያደራድሩ መዋላቸውም ታውቋል፡፡  

Read 6780 times