በሌላ በኩል የሆሊውድ ትልልቅ የአክሽን ተዋናዮችን ያሰባሰበበው “ዘ ኤክስፐንደብልስ” የተባለው አክሽን ፊልም ክፍል 2 ከሁለት ወር በኋላ ለእይታ ይበቃል፡፡ በፊልሙ ላይ ሲልቨስተር ስታሎን፤ ጄሰን ስታታም፤ጄት ሊ፤ ዶልፍላንድ ግሪን፤ አርኖልድ ሸዋዚንገር፤ ብሩስ ዊልስና ጂን ክላውድ ቫንዳም እንደሚተውኑ ታውቋል፡፡ በሲልቨስተር ስታሎንና በአሮንልድ ሽዋዚንገር ጥምረት የሚተወነው ሌላው የአክሽን ፊልም “ዘ ቶምብ” በቀረፃ ላይ እንደሆነም ተገልፃል፡፡ዘንድሮ በሆሊውድ ተሰርተው ለገበያ የቀረቡ የአክሽን ፊልሞች 570 እንደሚደርሱ የገለፀው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ፤ከ1990 ጀምሮ ባሉት 22 ዓመታት ከአክሽን ፊልሞች የተገኘው ገቢ 33 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቁሞ፤ አክሽን ፊልም ከኮሜዲ፤አድቬንቸርና ድራማ ፊልሞች ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይገልፃል፡፡