Monday, 03 June 2019 15:17

Blue Print (ብሉ ፕሪንት) ምንድነው?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

 Blue Print (ብሉ ፕሪንት) ሲባል ብዙ ሰው የሚያውቀው ወይንም የተለመደው በአብዛኛው ከቤት ስራ ፕላን ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ነገር ግን የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ማህበር ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ጋር ባለው ግንኙነት የማህጸንና ጽንስ አስተማሪዎች የብሉ ፕሪንት  አዘገጃጀትን በሚመለከት ስልጠና ሲወስዱ በምን መንገድ? ለምንስ ተግባራዊ ለማድረግ ነው? ከሚል የአምዱ አዘጋጅ ለአሰልጣኝና ለአንድ ሰልጣኝ ዶክተሮች ጥያቄ ስንዝራለች፡፡ በቅድሚያ አሰ ልጣኝ የነበሩት ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ የተናገሩትን ለአንባቢ ብለናል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ በኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሰው ኃይል ልማት የትምህርት ስልጠና ከፍተኛ አማካሪ ናቸው፡፡ በአለም አቀፉ ፕሮግራም በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር በመ ሆን የማህጸንና ጽንስ ትምህርት ቤቶችን በማገዝ ይሰራሉ፡፡ ዶ/ር ሰለሞን የሚ ከታተሉት የትም ህርት ጥራት ሲሆን ይህም ማለት ከመርሐ ግብሩ አንስቶ ክለሳ ማድረግ ፤ማሻሻል ፤ከዚያም ባለፈ የትምህርት ስርአቱ እንደተጻፈው መተግበሩን ለማረጋገጥ መምህራንን ማሰ ልጠንን ይጨ ምራል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ይሰጡ የነበረው ስልጠና የሚጀምረው ከማጸንና ጽንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ ጥሩ የትምህርት አሰጣጥ ምን መምሰል አለበት ፤መምህራኑ የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመው ትምህርቱን በቀላሉ ለተማ ሪዎች ማቅረብ እንዲችሉ ማገዝ (Teaching methodology) ትልቁ የሚተኮርበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ማስተማር ብቻ በራሱ በቂ አለመሆኑንና ትክ ክለኛው ትምህርት ተሰጥቶአል የሚባለውም ትክክለኛው ምዘና ሲካሔድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡  ስለሆነም በተማሪዎች ምዘና ላይም ስልጠናው ያተኩራል፡፡ ስልጠናው በመሰጠት ላይ ያለው በማህጸንና ጽንስ ሕክምና ላይ ትምህርትን ለሚሰጡ መምህራንና ሐኪሞች ሲሆን እስከአሁን ባለው ሂደትም በአስር ዩኒቨርሲቲዎች ላሉ መምህራን በአለም ላይ በመካሄድ ላይ ያሉ የሰለጠኑ  የማስተማሪያና የመመዘኛ ዘዴዎችን እንዲያውቁ ስልጠና ተካሂዶአል:: የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን በተመለከተ የትምህርት አሰጣጡም ሆነ ምዘናውን ለማሻሻል ኢትዮጵያ ውስጥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በጅማ ሆስፒታል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማስተርስ ዲግሪ ማስተማር ተጀም ሮአል፡፡
ሐኪሞች ብዙ ጊዜ ሕክምና መስጠትን እንጂ ማስተማርን እንደዋና ስራ አያዩትም የሚባል ነገር አለ ዶ/ር ሰለሞን እንደሚሉት፡፡ ማስተማርን በብዛት የምናመጣው በልምድ ነው እንጂ ስልጠና በመውሰድ አይደለም የሚል ትልቅ ክፍተት የሚፈጥር አስተሳሰብ በብዙዎች ዘንድ ቆይቶአል፡፡ በእርግጥ ይህ አስተሳሰብ በሕክምና ትምህርት ስልጠና ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች ምሩቃን ወዲያው ትምህርት ሲጨርሱ የማስተማር ስራ ይሰጣ ቸዋል እንጂ ለማስተማር ስራ ብቁ የሚያደርጋቸውን ክህሎት እንዲያገኙ አይደረጉም፡፡ ስለዚ ህም በሚያስ ተምሩበት ጊዜ ልምድን የሚያዳብሩት ከሚያዩት፤ ከሚሰሙት፤ ከመሰላቸው ነው እንጂ በሳይንሳዊ መንገድ በታገዘ መልኩ ትክክለኛ የማስተማር ዘዴ ተጠቅመው አይደለም፡፡
የተማሪዎች ምዘናን በተመለከተም ከላይ በማስተማር ሂደት ያለው ልምድ ተግባራዊ የሚደ ረግበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ አስተማሪዎቹ መመዘኛውን የሚያወጡት እራሳቸው ከሚያውቁትና ከመሰላቸው እንጂ ትክክለኛው መመዘኛ ምን መሆን አለበት በሚል በሳይንስ በተደገፈ መመሪያ ሲጠቀሙ አይታዩም፡፡ ስለዚህም እንደዋና ስራም አይቆጠርም፡፡ትምህርት በአግባቡ ካልተሰጠና ምዘናው በአግባቡ ካልተካሄደ ደግሞ በሂደቱ የሚያልፉ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን እውቀት አይጨብጡም፤ በትክክል ስላልተመዘኑም እውቀቱን መጨበጣቸው የሚጠታወቅበት ዘዴ የለም፡፡ ስለዚህም ሙያውን የሚቀላቀሉ ባለሙያዎች በተለያየ አቅምና ቁመና ላይ እንዲሆኑ ስለሚ ያግዝ ለህብረተሰቡ የሚሰጡትም አገልግሎት በዚያው ልክ የተለያየ እና ወጥ ያልሆነ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስለዚህም መምህራን ተማሪዎችን በተገቢው መንገድ እንዲያስተምሩ እና ተገቢውን ምዘና እንዲያካሂዱ ለማብቃት በተለያዩ መድረኮች ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ ከኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ከሚቺጋን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባካሄደው ስልጠና ተሳታፊዎች ከነበሩት መካከል ዶ/ር ወንድሙ ጉዱ በቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲ ካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር  ይገኙበታል፡፡ ይህ ስልጠና በማህጸንና ጽንስ ሕክምና በአስተማሪ ነት በስራ ላይ ላሉ ሐኪሞች ወይንም መምህራን የተዘጋጀ ሲሆን ብሉ ፕሪንት የሚባለ ውም ለተማሪዎች የሚዘጋጀውን ፈተና ወይንም መመዘኛ በስርአት በተደገፈ እና በአንድ አይነት መን ገድ ለማዘጋጀት የታለመ የስራ ላይ ስልጠና ነው፡፡
ዶ/ር ወንድሙ እንዳሉት ከአሁን ቀደምም ዩኒቨርሲቲዎቹ ትምህርቱንና ምዘናውን ወደማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ሙያ ለሚመጡ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ቀደም ያለው አሰራር ግን ወጥ በሆነ እና ደረጃውን በጠበቀ እንዲሁም ትምህርቱን ባማከለ መንገድ ሳይሆን ሁሉም ዩኒቨ ርሲቲዎች እና መምህራኖች በመሰላቸው መንገድ ምዘናውን የሚያወጡበት ሁኔታ ይስተዋል ነበር:: አሁን ግን ይህ ብሉ ፕሪንት የሚባለው አሰራር በምን መንገድ ተማሪዎቹን ማስተማርና መመዘን እንደሚገባ ልምድ የሚቀሰምበት ነው፡፡
ከአሁን ቀደም ስለነበረው አሰራር ዶ/ር ወንድሙ የሚከተለውን ምሳሌ ሰጥተዋል፡፡
‹‹ …ለምሳሌ ለማህጸን ሕክምና ልዩ ትምህርት የሚወስዱ የአራተኛ አመት ተማሪዎች ፈተና ይዘጋጅ ሲባል ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ጥያቄዎች ይውጡ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአስተ ማሪዎች ይከፋፈላል፡፡ አንድ አስተማሪ 20 ጥያቄ እንዲያወጣ ሌላው ደግሞ 30 ጥያቄ እንዲያወጣ…ወዘተ ሲከፋፈል አስተማሪዎቹ የመሰላቸውን ለራሳቸው በሚመቻ ቸው መንገድ ጥያቄ አውጥተው ያስረክባሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎቹ በትምህርት ያላገኙ ዋቸው ጥያቄዎች ሁሉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከየርእሶቹ ይህንን አይነት ወይንም ይህንን ያህል ጥያቄ ይውጣ የሚል ምንም አይነት መመሪያ አልነ በረውም፡፡ ስለዚህ ብሉ ፕሪንት የሚለው አሰራር ግን ከየትኛው አርእስት ጥያቄ ይውጣ? ከየርእሱ ምን ምን ያህል ጥያ ቄዎች ይውጡ? የሚለውንና በቀጣይ ማለትም ለወደፊት ለሚኖሩት አሰራሮ ችም ማሻ ሻያ ቢያስፈልግ የሚያገለግል ቋሚ የተማሪዎች ምዘና ሰነድ እንዲ ዘጋጅ የሚያ ደርግ ነው፡፡ ››  
ዶ/ር ወንድሙ አክለው እንደገለጹት በተለምዶ ብሉ ፕሪንት የሚባለው አንድ ቤት ሲሰራ በምን ያህል ካሬ ሜትር ስፋት፤ በምን ያህል ቁመት ፤ስንት ክፍሎች፤…ወዘተ በሚል ለያይቶ የሚያስ ቀምጥ ሲሆን መሐንዲሱ ቤቱን ከመሬት ለማስፈር ከተሰራው ፕላን ውጭ በየትኛውም አቅ ጣጫ የራሱን ፍላጎት የማይጨም ርበት  ቤቱ ሲሰራም ሆነ ከተሰራ በሁዋላ በቋሚነት በዶክመ ንትነት የሚቀመጥ ሰነድ ነው፡፡ በተማሪዎች ስልጠናና ምዘና ወቅትም ይህ ብሉ ፕሪንት ማለት
1/ እንደዶክመንት ይያዛል፡፡
2/ ምን ያህል ጥያቄ ይውጣ የሚለውን ይወስናል፡፡
3/ ከማህጸንና ጽንስ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የሚመዘኑባቸው ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው? የሚሉትን የሚይዝ እና መመሪያ የሚሆን ቋሚ ሰነድ እንዲዘጋጅ የሚያስችል ስልጠና ነው፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ በ12 ዩኒቨርሲቲዎች ከ1ኛ አመት እስከ አራተኛ አመት ያሉት የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ተማሪዎች ለጊዜው ኢሶግ እና የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኃላፊነት ጥያ ቄዎቹን እንዲያወጡና ምዘናውን እንዲያካሂዱ ከስምምነት ተደርሶአል፡፡ ለወደፊት ግን ዩኒቨርሲ ቲዎቹ የየራሳቸውን መመዘኛ እንዲያዘጋጁ እቅድ አለ፡፡
ይቀጥላል

Read 4726 times