Sunday, 02 June 2019 00:00

የዱከሙ ወጣት የመፃሕፍት ልገሳ እየጠየቀ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ቤተመፃሕፍት ለመክፈት አቅዷል

               በዱከም ከተማ ተወልዶ ያደገውና የቴኳንዶ መምህር ወጣት ኤርሚያስ አሻግሬ፤ ግለሰቦችና ተቋማት ማንኛውንም ዓይነት መፅሀፍት እንዲለግሱት ጠየቀ፡፡ በከተማዋ ለወጣቶች የተመቻቸ የመዝናኛም ሆነ የማንበቢያ ቦታ ባለመኖሩ ወጣቶች ለአጉል ባህርያትና ለሱስ መጋለጣቸውን የጠቆመው ወጣት ኤርምያስ፤ ለመታደግ ቤተ መፅሐፍት ለመክፈት ከራሱና በቅርብ ከሚያውቃቸው ወዳጅ ጓደኞቹ መፃሕፍቱ ማሰባሰብ መጀመሩን ገልፆ፤  እስካሁን ወደ 140 ያህል የተለያየ ይዘት ያላቸው መፅሀፍት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
“ጉዳዩን ለአጎቴ ልጅ አማክሬው የቤተ መፅሐፍቱን ዲዛይን ሊሰራልኝ ተስማምተናል” ያለው ወጣት ኤርያስም፣ ቦታውን ደግሞ ለዱከም ከተማ ከንቲባ ለማመልከት እንዳሰበና ለጥያቄው ምላሽ እንደማይነፍጉት እምነቱን ገልጿል፡፡ ለነዚህ ወጣቶች ህይወት መቃናት በጎ የሚያደርግ በስሙ በተከፈተው የፌስ ቡክ አካውንቱ በኩል በመገናኘት እንዲለግሱት ተማፅኗል፡፡ ወጣቱ በአሁኑ ወቅት በዱከም ከተማ፣ “ጊቦር ማርሻል አርትና ጂም” የተሰኘ ማሰልጠኛ ከፍቶ ከ45 በላይ ወጣቶችን በማሰልጠን ላይ የሚገኝ ሲሆን ከስፖርት አምልጠውኝ ወደሱስ የተዘፈቁትን ወደ ንባብ እንዲመለሱ ቤተ መፃህፍቱን ለማቋቋም ወሳኝ ነው ይላል፡፡

Read 2325 times