Sunday, 02 June 2019 00:00

‹‹የመንጋ ፍትህ መዘዝ›› በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በሩዋንዳ ከ25 ዓመታት በፊት የደረሰውን የዘር ማጥፋት የሚመለከት እውነተኛ ታሪክ  ‹‹የመንጋ ፍትህ መዘዝ ›› በሚል ርእስ በአማርኛ  ተተርጉሞ ለገበያ ቀርቧል፡፡
AN ORDINARY MAN በሚል ርእስ እውነተኛውን ታሪክ በመፅሃፍ ያቀረበው ሩዋንዳዊው ፖል ሩሴሳባቢጋና ነው፡፡  በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ በሚገኘው ሚሊ ኮሊን ሆቴል   ስራ አስኪያጅነት እየሰራ ፖል ሩሴሳባቢጋና ከ1268 በላይ ሰዎችን ከጭፍጨፋው አትርፏቸዋል፡፡
AN ORDINARY MAN የተሰኘውን መፅሃፍ ‹‹የመንጋ ፍትህ መዘዝ ›› በሚል ርእስ በ260 ገፆች ወደ አማርኛ የተረጎመው አቶ ጌታቸው አሻግሬ ነው፡፡  በመፅሃፉ መቅደም ላይ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው በዘር ላይ የተመሰረተ መተላለቅ ማብቂያው መቼ ይሆን የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ የትርጉም ስራውን መታሰቢያነትም ምን ባላሰቡት፤ ባልጠበቁትና ባልገመቱት ሁኔታ ህይወታቸውን ለተቀጠፉ፤ ምንም በማያውቁት ነገር ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናትና ከሞቀ ኑራቸው ለተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ይሁንልኝም ብሏል፡፡ በ160 ብር ለገበያ የቀረበውን ‹‹የመንጋ ፍትህ መዘዝ ››  ትንሳኤ ብርሃን ማተሚያ ቤት ያሳተመው ሲሆን በሁሉም መፅሃፍት መደብሮች ያገኙታል፡ ፡አቶ ጌታቸው አሻግሬ ከ2 ዓመት በፊት  በአሜሪካዊ ደራሲ ጆን ስቴንቤክ East of Eden በሚል የተፃፈው ረጅም  ልቦለድ  በአማርኛ ከ‹‹ገነት በስተምስራቅ›› በሚል ርዕስ  ተርጉሞ ለገበያ አቅርቦ ነበር፡፡

Read 2483 times