ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት 18ኛው ዙር የኪነ ጥበብ ምሽት፣ የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ ቤት) ያካሂዳል፡፡
“ጥበብ፣ ሕብር፣ ክብር ፍቅር” በሚል በሚቀርበው በዚህ የጥበብ ዝግጅት ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ፣ ፀሐፌ ተውኔት ሰዓዳ መሀመድ፣ አርቲስት ሚካኤል ታምሬ፣ አርቲስት ካሌብ ዋለልኝ፣ መምህርት ዕፀገነት ከበደ፣ አስታውሰኝ በነጋ፣ ሰዓሊና ገጣሚ በክሪ አህመዲን፣ ሚካኤል መኮንን፣ ክብሮም ገ/ማሪያምና መታሰቢያ ታለማ በመሶብ ባህላዊ ባንድ ታጅበው ስራዎቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡