Sunday, 02 June 2019 00:00

የኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ “የሚሊየነሩ ፍዳ” መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የአንጋፋው ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሉ “የሚሊየነሩ ፍዳ” የተሰኘ መፅሀፍ ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ የወጎችና ግጥሞች ስብስብ በያዘው በዚህ መፅሀፍ የምረቃ ሥነስርዓት ላይ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን ድምፃዊ ሀይለየሱስ ግርማ፣ “የባላገሩ አይዶል” አሸናፊው ዳዊት ፅጌ፣ ምናሉሽ ረታ፣ ሞገስ መብራቱ፣ መሳይ ተፈራ ካሳና ሌሎችም ዘፈኀግቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምሽት ኢትዮ ስፕሪንግ ባንድ ቫዮሊን ዳዊት ፍሬው ሀይሉም ክላርኔት ይጫወታሉ፡፡  አርቲስት ፍቃዱ ከበደ፣ ገነት ንጋቱ፣ ደራሲና ዳይሬክተር ፍፁም አስፋው፣ ገጣሚ ታገል ሰይፉ፣ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰና ሌሎች ራሱ ደረጀ ኃይሌ ከመጽሐፉ የተመረጡ ወጐችና ግጥሞች ለታዳሚው ያነባሉ ተብሏል፡፡
የመግቢያ ዋጋ መፅሀፉን መያዝ ብቻ ነውም ተብሏል፡፡ “የሚሊየነሩ ፍዳ” መፅሀፍ በ100 ገፆች ተቀንብቦ፤ በ59 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምርቃቱ ዕለት የሚሸጥበት ዋጋ እንደሚለይም ተገልጿል፡፡
ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሉ ከዚህ ቀደም “ትዝታ ሲጨለፍ” እና “አንዳንድ ነገሮችና ሌሎችም” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 228 times