Tuesday, 04 June 2019 00:00

ማሌዢያ 3 ሺህ ቶን የፕላስቲክ ቆሻሻ ወደመጣበት አገር ልትልክ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአለማችን በአካባቢ ብክለት በከፍተኛ ሁኔታ በመጠቃት ቀዳሚዋ አገር የሆነችው ማሌዢያ፤ ከተለያዩ አገራት በህገወጥ መንገድ ወደ ግዛቷ የገባ 3 ሺህ ቶን የሚመዝን የፕላስቲክ ቆሻሻ ወደመጣበት አገር መልሳ ልትልክ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የአገሪቱ የአካባቢ ሚኒስትር ባለፈው ማክሰኞ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ በብክለት የተማረረችዋ ማሌዢያ፤ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የፕላስቲክ ቆሻሻዎች፣ የእስያ አገራትን ጨምሮ ወደመጡባቸው የተለያዩ አገራት ለመላክ ወስናለች፡፡
በአገሪቱ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን መልሰው ጥቅም ላይ ያውሉ የነበሩ በርካታ ፋብሪካዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ፣ የፕላስቲክ ቆሻሻዎቹ ከፍተኛ የአካባቢ ብክለት እያስከተሉ እንደሚገኙ የጠቆመው ዘገባው፣ በህገወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ ወደ አገሪቱ የገባ 60 ኮንቴነር የፕላስቲክ ቆሻሻ ወደመጣበት አገር ለመመለስ መዘጋጀቷን አመልክቷል፡፡
አገሪቱ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ልትመልስባቸው ያቀደቻቸው አገራት 14 ያህል እንደሚሆኑ የጠቆመው ዘገባው፣ ከእነዚህም መካከል አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳና እንግሊዝ እንደሚገኙበት ገልጧል::


Read 1566 times