Monday, 03 June 2019 15:05

ሲንጋፖር ለህጻናት የተመቸች ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ናት ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)


         ሲንጋፖር ህጻናት ተገቢውን እንክብካቤ በማግኘት በጥሩ ሁኔታ የሚያድጉባትና ለህጻናት የተመቸች ቀዳሚዋ የአለማችን አገር መሆኗን አንድ አለማቀፍ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ሴቭ ዘችልድረን የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት፣ በ176 የአለማችን አገራት ላይ የሰራውን ጥናት መሰረት አድርጎ ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው አለማቀፍ የህጻናት አስተዳደግ ሁኔታ ሪፖርት መሰረት፤ ለህጻናት ምቹ በመሆን ስዊድን ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ፊንላንድ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ህጻናት ጤናና ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ሁኔታ፣ ለሞትና ለበሽታ የመዳረግ ዕድላቸውን፣ ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የመጋለጥ ዕድላቸውን ወዘተ በመገምገም የአገራቱን የህጻናት ምቹነት ደረጃ እንዳወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአለማችን 31 ሚሊዮን ያህል ህጻናት ተገድደው ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውንና 420 ሚሊዮን ያህል ተጨማሪ ህጻናትም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ አስከፊ ኑሮን እየገፉ እንደሚገኙ ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡

Read 1370 times