Friday, 24 May 2019 00:00

ግንቦት 20ን በድምቀት ለማክበር የታሰበ ነገር የለም ተባለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(6 votes)

በትግራይ ክልል በዓሉ ከወዲሁ መከበር ጀምሯል
                                         
             የደርግ መንግስት ከስልጣን ተወግዶ ኢህአዴግ አገሪቱን የተቆጣጠረበትን የግንቦት 20 በዓል ዘንድሮ በፌደራል ደረጃ በድምቀት ለማክበር አለመታሰቡንና በዓሉን በተመለከተ የወጣ ፕሮግራም እንደሌለ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ዘንድሮ ለ28ኛ ጊዜ የሚከበረው የግንቦት 20 በዓል። ባለፉት ዓመታት ከተለመደው በተለየ በተቀዛቀዘ ሁኔታ እንደሚከበርም እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በዓሉ በፌደራል ደረጃ ቀደም ሲል እንደሚደረገው በስቴዲዬም ወይም በህዝብ መሰብሰቢያ አደባባዮች ላይ በድምቀት ለማክበር አለመታሰቡን የጠቆሙት ምንጮች፤ በመንግስታዊ ተቋማት ውስጥ በጽዳት ዘመቻ፣ በፓናል ውይይትና በስብሰባዎች እንደሚከበር አመልክቷል፡፡
በበዓሉ ዕለት መንግስት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል በዓሉ በትግራይ ክልል ግንቦት 20 እንደወትሮው በድምቀት የሚከበር ሲሆን ከወዲሁ ከበዓሉ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Read 2463 times