Saturday, 25 May 2019 07:59

የእናቶች የምስጋናና የምረቃ ሥነ ሥርዓት ትላንት በኤሊየና ሞል ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ብጡል የሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ከኤሊያና ሆቴል ጋር በመተባበር “እማዬን በጋራ እናመስግን እንመርቅ” በሚል መሪ ቃል የእናቶች የምስጋና እና የምረቃ ሥነ ሥርዓት ትላንት በኤሊያና ሆቴል ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡
በሆቴልና በተለያዩ ኪነ-ጥበብ ሥራዎች አማካሪነት ላይ የተሰማራው ብጡል የሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ፕሮግራሙን የዘንድሮውን ፕሮግራም ያዘጋጀው ኃላፊነታቸውን ተወጥተው በተለያዩ ዘርፎች ተሰልፈው ውጤታማ የሆኑ፣ የእንክብካቤ፣ የፍቅር፣ የመሳሰብና የአንድነት ተምሳሌት የሆኑት የኢትዮጵያ እናቶችን ለማመስገን ሲሆን በዕለቱም እናቶች ተመስግነዋል ተመርቀዋል፡፡ አዘጋጁ ድርጅት በቀጣይም የአገር ምሰሶ የሆኑ እናቶችን በየአመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር ለታዳሚ አስታውቋል፡፡

Read 1642 times