Saturday, 18 May 2019 00:00

“መፍትሔው ኢትዮጵያዊነት ነው” የኪነ-ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን ተዘጋጅቶ የሚቀርበው የኪነጥበብ ምሽት የፊታችን ማክሰኞ 11 ሰዓት ጀምሮ “መፍትሔው ኢትዮጵያዊነት ነው” በሚል ርዕስ በብሔራዊ ቴአትር ይቀርባል፡፡
 በምሽቱ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉና ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን የ “ማማ በሰማይ” ደራሲ ህይወት ተፈራ፣ አርቲስት አለማየሁ ታደሰና አርቲስት ሽመልስ አበራ ወግ ያቀርባሉ፡፡
ገጣሚ ነቢይ መኮንንና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ደግሞ የግጥም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ተመን ያላቸው 100 ብር ትኬቶቹ በዮናስ መጽሐፍት መደብር፤ በጃፋር መጽሐፍት መደብር በአይናለም መጽሐፍት መደብር፣ በጣይቱ ሆቴልና ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት እንደሚሸጡ ተጠቁሟል፡፡ ምሽቱ በፊደል የሙዚቃ ባንድ እንደሚታጀብም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 5763 times