Tuesday, 21 May 2019 12:17

የሞኔት ስዕል በ8 ደቂቃ ጨረታ 110.7 ሚ. ዶላር ተሸጠ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አማዞን በ1.5 ቢሊዮን ዶላር አውሮፕላን ማረፊያ እየገነባ ነው

                የታዋቂው ሰዓሊ ክላውድ ስራ የሆነውና “ሚዩሌስ” የተሰኘው ጥንታዊ ስዕል፣ 8 ደቂቃ ብቻ በፈጀ ጨረታ ክብረ ወሰን ባስመዘገበ ዋጋ 110.7 ሚ. ዶላር መሸጡ ተዘግቧል፡፡
እ.ኤ.አ በ1890 የተሳለውና ከፈረንሳዊው ሰዓሊ ምርጥ ስራዎች አንዱ እንደሆነ የተነገረለት ይሄ ስዕል ባለፈው ማክሰኞ ሲዝቤይ በተባለው አጫራች ኩባንያ አማካይነት ኒው ዮርክ ውስጥ ለጨረታ ቀርቦ መሸጡንና በአለማችን በኢምፕሬሽኒስት ዘዬ ከተሳሉ ስዕሎች በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን ነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዘገበው፡፡
55 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሎ የተገመተውን ይህን የዘይት ቀለም ስዕል ለመግዛት ስድስት ተጫራቾች መቅረባቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ስሙና ማንነቱ ያልተገለጸው አንደኛው ተጫራች ከተገመተው በእጥፍ ያህል የሚበልጥ ዋጋ በማቅረብና በማሸነፍ ስዕሉን በእጁ ማስገባቱን አመልክቷል፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ፣ የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር የጄፍ ቤዞስ ኩባንያ አማዞን፣ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ መገንባት መጀመሩን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ የተለያዩ ሸቀጦችን በአለም ዙሪያ በማድረስ ከአለማችን ኩባንያዎች ቀዳሚነቱን የያዘው አማዞን፤ አገልግሎቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ በማሰብ በኬንተኪ የራሱን ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ባለፈው ሰኞ መገንባት ጀምሯል፡፡

Read 1191 times