Print this page
Saturday, 11 May 2019 00:00

ኢ/ር ታከለ ኡማ በአሜሪካ የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ሊወያዩ ነው

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(2 votes)


ኢ/ር ታከለ ኡማ በአሜሪካ የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ዛሬ ሊወያዩ ነው
በአሜሪካ የስራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ መስተዳደር ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ ለሚገኙ የዲያስፖራ የሙያ ማህበር እና ተቋማት ባለቤቶች እና አባላቶች ጋር ተወያይቶ የስራ ውጤት ማከናወኛ የሚሆን ቢሮ በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ የሚያስችል ውይይት ያካሂዳሉ ተባለ፡፡
ውይይቱ የሚያተኩረው በአሜሪካ በተለያዩ የሙያ ተቋማትን አቋቁመው እየሰሩ የሚገኙ ኢትዮጵያንን በማበረታታት በስራቸው በሙያቸው አገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማስቻል እና እንደከዚህ ቀደም ዲያስፖራውን ሰብስቦ የማወያየት ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ሆነው ስራቸውን የሚሰሩበት መንገድ ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አገራቸው እየመጡ በሙያቸው የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለኢ/ር ታከለ ጥያቄ ማቅረባቸውን የተገለፀ ሲሆን በዩንቨርስቲ የሚማሩ የሚያስተምሩ እና በልዩ ፈጠራ ስመ ጥር የሆኑ ኢትዮጵያኖች አገራቸውን በአቅማቸው ለመደገፍ መነሳታቸው ተገልጿል፡፡
ዛሬ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ያሉ ኢትዮጵያውያን ቅርንጫፎች ከፍተው ስራቸውን እንዲሰሩ የሚያስችል ውይይት በማድረግ እንዴት ወደ ተግባር መሄድ ይቻላል? በሚለው ላይም ውሳኔ እንደሚያሳልፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 877 times