Saturday, 11 May 2019 14:55

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ “ከገባንበት መውጫ” መጽሐፍ ለገበያ ቀርቧል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


       “ከገባንበት መውጫ” የተሰኘው የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ አራተኛ መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀረበ፡፡ መጽሐፉ በሀገሪቱ የተጋረጡ የትርምስ ቀውሶችንና የፖለቲካ ሸፍጦችን መወጣት የሚቻልባቸውን መንገዶች በልሂቃን ትንታኔ የሚያመላክት መሆኑን ደራሲው አስታውቋል፡፡ ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ እንድትገባ ያደረጉ አስተሳሰቦችና ሳይንሳዊ መፍትሔዎቻቸውንም በታዋቂ የፖለቲካ ልሂቃንና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ትንታኔ አስደግፎ ያቀርባል - መጽሐፉ፡፡ ጋዜጠኛ ወብሸት ታዬ በጋዜጠኝነት ሙያው የሁለት ታላላቅ አለማቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት “የነፃነት ድምፆች”፣ “ሞጋች እውነቶች” እና “ኢትዮጵያዊነትን “የመመለስ ተጋድሎ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለአንባቢያን ማቅረቡ ይታወሳል::

Read 10820 times