Monday, 13 May 2019 00:00

የ7ኛው ዙር “የበጐ ሰው ሽልማት” እጩዎች ጥቆማ ተጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


               ለሀገርና ለህዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን እውቅና የሚሰጠው “የበጐ ሰው ሽልማት” ሰባተኛው ዙር የእጩዎች ጥቆማ በትላንትናው እለት መጀመሩን የሽልማቱ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ኮሚቴው ሀሙስ ከሰዓት በኋላ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ዘንድሮ በ10 ዘርፎች ለአገርና ለህዝብ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉና ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ በጐዎችን እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ዘርፎቹም በሳይንስ (በህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ምህንድስና፣ አርክቴክቸር ወዘተ…)፣ በኪነ ጥበብ (በሥነ -ጥበብና ፎቶግራፍ)፣ በበጐ አድራጐት (እርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት)፣ በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ፣ በመንግስታዊ የስራ ተቋማት ኃላፊነት፣ በቅርስና ባህል፣ በማህበራዊ ጥናት፣ በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ “ለኢትዮጵያ በጐ ያደረጉ የውጭ ዜጐች” የሚለው ዘርፍ ተጠቋሚዎች እያነሱ በመምጣታቸው ዘንድሮ “ለኢትዮጵያ እድገት ያበረከቱ ዲያስፖራዎች” በሚል መተካቱም ተጠቁሟል፡፡ የሽልማት ሥነ - ሥርዓቱ ነሐሴ 26 ቀን 2011ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

Read 9639 times