የአልኮል ተጠቃሚነት በ27 አመታት 70 በመቶ ጨምሯል
የአልኮል ተጠቃሚነት በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝና ባለፉት 27 አመታት ጊዜ ውስጥ የአልኮል ተጠቃሚነት በ70 በመቶ ያህል መጨመሩን አንድ አለማቀፍ ጥናት አመለከተ፡፡
አንድ የጀርመን ተቋም በአለማችን 189 አገራት ላይ የሰራውን ጥናት ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ በፈረንጆች አመት 2017 ብቻ በመላው አለም 35 ሺህ 676 ቢሊዮን ሊትር አልኮል ተጠጥቷል፡፡ ባለፉት 27 አመታት የአልኮል ተጠቃሚነት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በእስያ አገራት እንደሆነ የጠቆመው ጥናቱ፤ አነስተኛ አልኮል የሚጠቀሙት ደግሞ አውሮፓውያን መሆናቸውን አመልክቷል፡፡
የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚነት በመላው አለም በርካታ ሰዎችን ለተለያዩ የጤና ችግሮች በመዳረግ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ መሆኑንና ከ200 በላይ በሽታዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ያመለከተው ዘገባው፤ የአለም የጤና ድርጅት በበኩሉ በፈረንጆች አመት 2016 ብቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አልኮል አብዝተው በመጠጣታቸው ሳቢያ ለሞት እንደተዳረጉ ማስታወቁን አስታውሷል፡፡
የአልኮል ተጠቃሚነት በተለይ በወጣቶች ዘንድ እየተስፋፋ እንደሚገኝና በመጪዎቹ አስር አመታት ጊዜ ውስጥ ከአለማችን ወጣቶች መካከል ግማሹ አልኮል ጠጪዎች ይሆናሉ ተብሎ እንደሚገመትም ጥናቱ አክሎ ገልጧል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል