Saturday, 04 May 2019 15:15

“ኢትዮ ኤርትራ” የስዕል ኤግዚቢሽን ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ከ20 ዓመታት በላይ ተለይተው የነበሩትን የሁለቱን አገራት ዳግም ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ያደርሳል ተብሎ የታመነበት “ኢትዮ-ኤርትራ” የስዕል አውደርዕይ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ከምሽቱ 11፡30 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው “ፈንዲቃ የባህል ማዕከል” መከፈቱን የዝግጅቱ አስተባባሪ ገሳ ኢቨንት ኦርጋናየዘርና ፕሮሞሽን አስታወቀ፡፡
በአውደ ርዕዩ በኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ብርሃን በየነና በኤርትራዊው ሰዓሊ ነባይ አብርሃ የተሳሉና የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያንፀባርቁ ከ30 በላይ ሥዕሎች ለእይታ ቀርበውበታል፡፡
በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ በርካታ ሰዓሊያን የጥበብ አፍቃሪያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን የስዕል ሥራዎቹ ለ3 ሳምንታት ለእታ ክፍት ሆነው እንደሚቆዩ ታውቋል፡፡፡

Read 6049 times