Print this page
Saturday, 27 April 2019 10:32

በ20 ሚ.ብር የተገነባው “ሚዩዚክ ሪቮሊዩሽን” መዝናኛ ማዕከል ሊመረቅ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የአሜሪካው ሲኢኦ፣ የአዲስ አበባው ሲኢኦ ቁጥር ሁለት፣ የሰሬንደርና “የፉድ ዞን” እህት ኩባንያ የሆነውና የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ ለማዘመን ታስቦ በ20 ሚ. ብር የተገነባው “ሚዩዚክ ሪቮሊዩሽን” የምሽት መዝናኛ ክለብ ሊመረቅ ነው፡፡ ከአትላስ አለፍ ብሎ በሚገኘው ሸገር ሀውስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ የተገነባው የመዝናኛ ክበቡ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ በዓለም ላይ አሉ የተባሉ የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑት የመብራትና የድምጽ ሲስተሞች እንዲሁም የተመልካችን አይን በማይረብሹ ከ16 በላይ ቀለማትን ማውጣት በሚችሉ ኤልኢዲ መብራቶች የተደራጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ለ100 ያህል ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረው የምሽት መዝናኛ ክለቡ በከተማችን የሚገኙ ስመጥር ወጣትና አንጋፋ ድምፃዊያን ዓለምአቀፍ ይዘቱን በጠበቀና በኤክስፋክተር አሜሪካን አይዶል ደረጃ በታነፀ አንፀባራቂ መድረክ ላይ ሥራዎቻቸውን ለአድናቂዎቻቸው በቋሚነት ያቀርቡበታል የተባለ ሲሆን፤ የአገራችንና የውጭ ሙዚቀኞች በማጣመር የሙያ ክህሎታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ይሆናልም ተብሏል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትና የሙዩዚክ ሪቮሊዩሽንን ባለንብረት ባለሀብቶች በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው ሲሆኑ በአሜሪካና በአውሮፓ ትልልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ሲያዘጋጁ እንዲቆዩም ታውቋል፡፡ ሚዩዚክ ሪቮሊዩሽን ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ምሽት ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ከሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ሐሙስ ምሽት ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የቀይ ምንጣፍ የምረቃ ስነ ሥርዓት እንደሚኖረው ታውቋል፡፡

Read 11367 times