Print this page
Saturday, 27 April 2019 10:30

“ሰምና ወርቅ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በየወሩ የሚካሄደው “የሰምና ወርቅ” የኪነጥበብ ምሽት 17ኛው ዙር የፊታችን ሀሙስ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ይካሄዳል፡፡ በእለቱም ዶ/ር ብርሃኑ ኃ/ሚካኤል፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ፣ አንጋፋው ገጣሚ ወንድዬ አሊ፣ የስፖርት ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ (ኦያያ) እና መምህርት እፀገነት ከበደ፣ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ፣ ተሾመ ብርሃኑ፣ ዮፍታሄ
ብርሃኔ ቶማስ አድማሱ፣ ኤልሳ ሙሉጌታና የአብስራ አሰፋ በመሶብ የባህል ቡድን ታጅበው ሥራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡


Read 6007 times