Print this page
Saturday, 20 April 2019 14:08

13ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በኢንሺየቲቭ አፍሪካ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚቀርበው  13ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ከሚያዚያ 22-27 ቀን 2011 ዓ.ም በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡ የዘንድሮውም ፌስቲቫል እንደከዚህ ቀደሙ ለሰው ልጆች ኑሮ ህልውና አስጊ በሆኑ ጉዳዮች ማለትም በማህበራዊ ፍትህ፣ ግላዊና ማህበረሰባዊ ልዩነቶች፣ በአካባቢ ብክለት፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰሩ ወደ 600 የሚጠጉ ዘጋቢ ፊልሞች ከመላው ዓለም ለውድድር ቀርበው የተመረጡት 60 ያህሎቹ ለእይታ የሚቀርቡበት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡ በፊልም ፌስቲቫሉ  ለአገራችን ፊልም ሰሪዎች ጠቃሚ የሆነ የልምድ ልውውጥ፣ ሴሚናርና ሌሎች ትምህርታዊ መድረኮችም እንደሚኖሩ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ከ500 በላይ ዘጋቢ ፊልሞችን አወዳድሮ ለእይታ ማብቃቱን ያስታወሰው ኢንሺየቲቭ አፍሪካ፤ የዘንድሮውን የፊልም ፌስቲቫል ዝርዝር ሁኔታ በተመለከተም የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Read 5770 times