Saturday, 13 April 2019 13:55

“5ኛው ግጥም በበገና” የስነ ፅሁፍ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


             “ግጥም በበገና” አምስተኛ ዙር የስነ ፅሁፍ ምሽት የፊታችን አርብ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ እንደሚካሄድ ኢጋ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ፡፡ በምሽቱ የበገና ድርደራ፣ የክራር ገረፋ፣ ግጥም፣ ህብረ ዝማሬ፣ ግለ ወግና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የህፃናትና የአዋቂ የንባብ ባህልን በማዳበር፣ ባህላዊና አገራዊ እሴቶችን በማጉላትና በተለያዩ የማንነታችን መገለጫዎቻችን እንድንኮራ የሚያደርጉ ፋይዳ ያላቸውን ስራዎች በመስራት የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡

Read 5951 times