Saturday, 13 April 2019 13:48

“ባትፈልገኝ እፈልግሃለሁ” መፅሐፍ ተመርቆ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የፕሬዚዳንት መሀመድ ዚያድ ባሬ መራሹን ጦር ለመመከት የተሰማራው የ3ኛ ፓራ ኮማንዱ ብርጌድ ጦር አባል በነበሩትና በጦርነቱ ከተዋጉት አንዱ በሆኑት ደራሲ ሊባኖስ ገዳሙ የተፃፈው “ባትፈልገኝ እፈልግሃለሁ” የተሰኘ መፅሐፍ የዛሬ ሳምንት በወመዘክር ተመርቆ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የወቅቱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ “ታላቋ ሶማሊያን” ለመገንባት የነበረው ህልም እውን ለማድረግ በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያን የተወሰነ ክፍል በቁጥጥሩ ስር አድርጐ በነበረበት ጊዜ በአጭር ጊዜ የተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦር፤ ወረራውን ለመቀልበስ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰና
አጠቃላይ ሂደቱን ያስቃኛል፡፡ ደራሲውና ለግዳጅ ወደ ምስራቅ ሲሄድ ያገኛት ወጣት የፍቅር ጅማሮና ሂደትን የሚያስቃኘው መጽሐፉ፤ በ414 ገፅ የተቀነበበ ሲሆን በ150 ብር፣ በ20 ዶላር፣ በ20 ዩሮና በ20 የካናዳ ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 739 times