Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 02 June 2012 08:54

ቤሩት የሞተችው ወጣት ባለቤት ዘገባዎችን አስተባበለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ቤይሩት ውስጥ ለህክምና በገባችበት ሆስፒታል በአንሶላ ቅዳጅ ታንቃ ህይወቷ ያለፈውና አስከሬኗ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ያልመጣው የወ/ሮ አለም ደቻሳ የቀድሞ ባለቤት፤ ታናሽ ወንድሙዋ ስለእኔና ስለእሱዋ የተናገረው ከእውነት የራቀና አንድም ተጨባጭ እውነት የሌለው ነው ሲል አስተባበለ፡፡ የወ/ሮ አለም ደቻሳ ታናሽ ወንድም ለታ ደቻሳ፤ እህቱ ወደ ቤሩት ስትሄድ አስር ሺህ ብር በብድር ሰጥቷት እንደነበር የገለፀው ፈፅሞ ሃሰት ነው ያለው አቶ ለሜሳ እጀታ፤ገንዘቡን ያገኘነው ከተለያዩ ቦታዎች ጥረት አድርገንና  በጋራ ተደራድረን ነው ብሏል፡፡ ለአስራ አራት አመት ከእህቱ ጋር በትዳር ስንኖር አንድም ቀን እቤታችን መጥቶ መጥቶ የማያውቀው ይሄ ሰው፤ሁሌም ሲጣሉ የማስታርቃቸው እኔ ነበርኩ ማለቱ በእጅጉ አሳዝኖኛል ብሏል - አቶ ለሜሳ፡፡ “ገና ለገና ካሣ አገኛለሁ በሚል ስሜን ለማጥፋት አይችሉም” ሲልም ተናግሯል፡፡

በጋብቻ ላይ በፈፀመው ጋብቻ አንድ ልጅ መውለዱን የገለፀው አቶ ለሜሳ፤ ይህንኑ ጉዳይ ወ/ሮ ዓለም እንደምታውቅና እንደውም አለምና አዲሲቱ ሚስቱ በጣም የሚቀራረቡና የሚዋደዱ ሰዎች እንደነበሩ ተናግሯል፡፡ በወለደች ጊዜ ዓለም ራሷ እየሄደች ትጠይቃት ነበር ያለው አቶ ለሜሳ፤ ቤት ተከራይቼ እንዳስቀምጣት ሃሳብ የሰጠችኝም እራሷ ዓለም ነበረች ብሏል፡፡ ወደ አረብ አገር የሄደችው እኔ ከሌላ መውለዴን ሰምታ በንዴት ነው የሚለውን ሃሣብ ፈፅሞ እንደማይቀበለው የገለፀው አቶ ለሜሳ፤ በሰፈራችን ከሰባት በላይ ሰዎች ወደ አረብ አገር ሄደው  የተሻለ ኑሮ መጀመራቸውን ስታይና ከገበሬ ላይ በገዛናት 200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሁለት ክፍል ቆርቆሮ ቤት በመሥራት ከቤት ኪራይ ለመገላገል ባላት ህልም ነበር ከአገሯ የወጣችው ሲል አስተባብሏል፡፡

 

 

 

Read 4010 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 09:02